1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰማያዊ ፓርቲ አባል እና የአዲስ ጉዳይ የፎቶ ጋዜጠኛ ችሎት

ረቡዕ፣ ሐምሌ 30 2006

በሜክሲኮ አደባባይ የሚገኘው የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባለፈው የረመዳን ጾም ወቅት በአንዋር መስጊድ በተካሄደው ረብሻ ላይ ተሳትፋችኋል በሚል የተጠረጠሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወይንሸት ሞላን እና የአዲስ ጉዳይ የፎቶ ጋዜጠኛ

https://p.dw.com/p/1CpgW
Symbolbild Hammer Gericht
ምስል Fotolia/Gina Sanders

አዚዛን ጉዳይ ትናንት ተመልክቶ በአምሥት ሺህ ብር ዋስትና እንዲወጡ ብይን አስተላልፎ ነበር። ይሁንና፣ ፖሊስ ይግባኝ በማለቱ ፍርድ ቤቱ ተከሳሾች ከእስር ቤት ሳይወጡ የምርመራው ሂደት በ,ተከታዮቹ ሰባት ቀናት እንዲካሄድ ወስኖዋል። በተያያዘ ዜናም፣ ከግንቦት ሰባት እና ከኢሳት ጋ ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩት በእስር የሚገኙት የአንድነት፣ የሰማያዊ ፓርቲ እና የአረና አመራር አባላት አራዳ በሚገኘው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ችሎት ቀርበው እንደነበር እና ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ያቀረበውን የ28 የምርመራ ቀናት ጥያቄ ተቀብሎ ለነሀሴ 27 ተለዋጭ ቀጠሮ እንደሰጠ ተሰምቷል ።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ