1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰማያዊ ፓርቲ ጥያቄ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 4 2010

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሽፋን በኦሮምያ ክልል በቦረና ዞን በሞያሌ ከተማ በንጹሀን ዜጎች ላይ የተፈፀመው ግድያ የሚመለከታቸው ሁሉ በሕግ እንዲጠየቁም ጥሪ አስተላልፏል። አገራዊ መግባባት ላይ መድረስ ያስችላሉ ያላቸውን ቅድመ ሁኔታዎችንም ዘርዝሯል።

https://p.dw.com/p/2uGMn
Äthiopien Oppositionspartei Blue Party - Pressekonferenz Addis Abeba
ምስል DW/G. Tedla HG

የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ

ተቃዋሚው ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተነስቶ ሀገሪቱ ወደ ቀድሞው የሕግ ማስከበር ስርዓት እንድትመለስ ጠየቀ። ፓርቲው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ህዝቡን በጠመንጃ ማስፈራራቱን ትቶ ከህዝብ ጋር እርቅ እንዲያወርድ ጠይቋል። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሽፋን በኦሮምያ ክልል በቦረና ዞን በሞያሌ ከተማ በንጹሀን ዜጎች ላይ የተፈፀመው ግድያ የሚመለከታቸው ሁሉ በሕግ እንዲጠየቁም ጥሪ አስተላልፏል። አገራዊ መግባባት ላይ መድረስ ያስችላሉ ያላቸውን ቅድመ ሁኔታዎችንም ዘርዝሯል። ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል።


ጌታቸው ተድላ ኅይለ ጊዮርጊስ


ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ