1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰሜኑ ንፍቀ ክበብ ክረምትና የ2010 ቅኝት

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 12 2003

የሰሜን ንፍቀ ክበብ የክረምት ወራት ዉጭ ባይወጣስ በሚያሰኘዉ ቆንጣጭ ቅዝቃዜዉ፤

https://p.dw.com/p/Qi13
የሰሜኑ ንፍቀ ክበብ ክረምንትና የበረዶ ጭቃምስል dapd

ያንንም ከሚያጠናክረዉ ሲያሻዉ እንደባለሙያ ባዘቶ አለያም እንደአሸዋ ድምጽ ሳያሰማ ዙሪያ ገባዉን ወተት የተደፋበት በሚያስመስለዉ በረዶዉ አጅቦ የዘመን ወር ተራዉን ተያይዞታል። በረዶዉ ተጠናክሮ መዉረድ የጀመረዉ ገና ክረምቱ ግም ከማለቱ ቢሆንም የሰሞኑ ደግሞ የየብስም ሆነ የአየር መጓጓዣዎችን እያስተጓጎለ ነዉ። የሎንዶን፤ ፍራንክፈርት፤ አምስተርዳምና ብራስልስ አዉሮፕላን ማረፊያዎች በረዶ እየጠረጉ በረራዎችን ለማስተናገድ ቢጥሩም በጀርመን ብቻ አራት አዉሮፕላን ማረፊያዎች ከአንድ ሺ በላይ በረራዎች ለመሰረዝ ተገደዋል። ይህም በርካታ መንገደኞች በየአዉሮፕላንና ባቡር ጣቢያዉ ከነጓዛቸዉ እንዲንገላቱ አድርጓል። ዙሪያ ገባዉን ያለበሰዉ በረዶ የተሽካርካሪ አደጋም ሆነ የጤና እክልን ብሎም ህልፈተ ህይወትን እያስከተለ መሆኑ ቢሰማም፤ በዚህ በምዕራቡ ዓለም ደምቆ የሚከበረዉን የገና በዓል ማጀቡን ግን የጠላ የለም። እንደዉም እነሱ ኋይት ክሪስመስ ማለትም ነጭ ገና የሚሉትን በበረዶ የታጀበ በዓል ዘንድሮ እንደሚያከብሩ እርግጠኛ ሆነዋል። ተፈጥሮን ተቀብሎ መኖር ይሏል ይኸዉ ነዉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ