1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን በዋርሶ

ዓርብ፣ ሐምሌ 1 2008

የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን በእንግሊዝኛ ምህጻሩ ኔቶ አባል ሃገራት መሪዎች አንዳቸዉ ሌላቸዉን በወታደራዊ ኃይል ለመደገፍ አቅማቸዉን ማጠናከር እንደሚኖርባቸዉ የድርጅቱ ዋና ፀሐፊ አመለከቱ።

https://p.dw.com/p/1JLpL
NATO Gipfel in Warschau Treffen an die Marginen Obama mit Tusk und Juncker
ምስል Getty Images/AFP/M. Ngan

[No title]

የ28 ነፃ መንግሥታት ትብብር የሆነዉ ኔቶ አባል ሃገራት መሪዎች ዛሬ በዋርሶ ፖላንድ ተገናኝተዉ በአባል ሃገራትና ዜጎች ላይ የተደቀነ ያሉትን አደጋ በሚከላከሉበት ስልት ላይ እየመከሩ ነዉ። የዉይይታቸዉ ትኩረትም በተለይ አልመች ያለችዉ ወታደራዊ ጦር ኃይሏ የተጠናከረዉ ሩሲያ እና አመፅ የተቀላቀለዉ የሙስሊም ፅንፈኝነት ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ የአሶሲየትድ ፕረስ ዘገባ ያመለክታል። የኔቶ ዋና ጸሐፊ የንስ ሽቶልተንበርግ በዉይይታቸዉ የአዉሮጳ እና የሰሜን አሜሪካን ትብብር ዳግም በማረጋገጥ በማንኛዉም የስጋት ወቅት በጋራ ለመንቀሳቀስ መሆኑን ገልጸዋል። አክለዉም፤

«በባልቲክ ሃገራት አካባቢ እና በፖላንድ ወታደራዊ እንቅስቃሴያችንን እናጠናክራለን፤ ነገር ግን ሩሲያ ዩክሬን ዉስጥ ላደረገችዉ አንዳች ምላሽ ሳንሰጥ እንደማንቀር ጥርጥር የለም። ዩክሬን ዉስጥ ከመደረጉም ሆነ ክሬሚያ በሕገወጥ መንገድ ከመገንጠሏ በፊት እንዲህ ዓይነት ወታደራዊ እንቅስቃሴ ፖላንድ ዉስጥም ሆነ በባልቲክ ሃገራት እንዲኖር በሚል ማንም አልተነጋገረም ነበር። እናም አሁን የምናደርገዉ መከላከል ነዉ። የተመጣጠነ እና ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰባችን ጋር የተስማማ ነዉ። በተጨማሪም ሩሲያ ከምትወስደዉ የትኛዉም ምላሽ የሚስተካከል ነዉ ምክንያቱም በየትኛዉም መንገድ ኔቶ የሚወስደዉ ርምጃ የመከላከል ነዉ።»

በወታደራዊ ኃይሏ ሉአላዊ ሃገራት ላይ ሕገወጥ ርምጃ የምትወስድ ሩሲያን እየተመለከትን ነዉ ያሉት ዋና ጸሐፊ አክለዉም ክሬሚያየ ከዩክሬንበመገንጠሏ ድርጅታቸዉ በተጠቀሰዉ አካባቢ ኃይሉን ለማጠናከር መወሰኑን አመልክተዋል። የአባል ሃገራት የፀጥታ ኃይሎችን ማሰልጠንም የኔቶ ዋና ተግባር መሆኑንም ገልጸዋል። በጉባኤዉ ላይ የተገኙት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማም በድርጅቱ ስር 1 ሺህ የአሜሪካን ወታደሮች ፖላንድ ዉስጥ እንደሚሰማሩ አስታዉቀዋል።

NATO Gipfel in Warschau Global Hawk Drohne vor dem Veranstaltungsort
ምስል picture-alliance/dpa/R. Jensen

የሚኒስትሮችና የጦር ባለሙያዎች ሥብሰባ ላይ እንደተነገረዉ መሪዎቹ ሩሲያን በሚያዋስኑ የድርጅቱ አባል ሐገራት አዲስ ጦር ሐይል እንዲሰፍር ይወስናሉ ተብሎ ይጠበቃል።ጉባኤተኞቹ ከዚሕም በተጨማሪ የኢራቅና የሶሪያ እስላማዊ መንግሥት (ISIS)ን ለማጥፋት የተከፈተዉን ዘመቻ ለማጠናከር ድርጅቱ በራሪ ራዳሮችን እንዲያዘምት ይወስናሉ።

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) አባል ሐገራት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ማምሻዉን ዎርሶ-ፖላንድ ዉስጥ ተጀምሯል።ከመሪዎቹ ጉባኤ በፊት በተደረገዉ የሚኒስትሮችና የጦር ባለሙያዎች ሥብሰባ ላይ እንደተነገረዉ መሪዎቹ ሩሲያን በሚያዋስኑ የድርጅቱ አባል ሐገራት፤ አዲስ ጦር ሐይል እንዲሰፍር ይወስናሉ ተብሎ ይጠበቃል።ጉባኤተኞቹ ከዚሕም በተጨማሪ የኢራቅና የሶሪያ እስላማዊ መንግሥት (ISIS)ን ለማጥፋት የተከፈተዉን ዘመቻ ለማጠናከር ድርጅቱ በራሪ ራዳሮችን እንዲያዘምት ይወስናሉ።ኔቶ ሩሲያ አዋሳኝ ድንበር ላይ ጦር ለማስፈር ማቀዱን ሞስኮ አጥብቃ ተቃዉማዋለች።ሥለ ጉባኤና ዕቅዱ የዎርሶ ተባባሪ ዘጋቢያችንን ስለሺ ይልማን በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ሺበሺ ይልማ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ