1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ምርጫና ተቃውሞ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 4 2005

ለተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት ክፍት መቀመጫዎች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ትናንት በተካሄደ ምርጫ ከአፍሪቃ ከእስያ ና ከላቲን አሜሪካ ቡድን በሰብአዊ መብት ጥሰት በሚከሰሱ አገራት ጭምር መያዛቸው እያነጋገረ ነው ።

https://p.dw.com/p/16iim
UN Secretary General Ban Ki-moon looks on prior to address the twenty-first session of the UN Human Rights Council on September 10, 2012 at the United Nations offices in Geneva. Ban and his human rights chief Navi Pillay called for more accountability for the bloodshed in Syria. AFP PHOTO / FABRICE COFFRINI (Photo credit should read FABRICE COFFRINI/AFP/GettyImages)
ምስል Getty Images

ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት አባልነት የሚካሄዱ ፉክክራቸው የተገደበ ምርጫዎች የመንግሥታቱ ድርጅት ለምክርቤቱ አባልነት ላስቀመጣቸው ደረጃዎች ትኩረት ያልሰጡ ናቸው ሲል ሂዩመን ራይትስ ዋች ወቀሰ ። አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ሂዩመን ራይትስ ዋች በምክርቤቱ የምርጫ ስርዓት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት የሚፈፅሙ ያላቸው እንደ ኢትዮጵያ የመሳሰሉ የአፍሪቃ ሃገራት በአባልነት መመረጣቸውን በፅኑ ተቃውሟል ። የድርጅቱን የ ጂኒቫ ቢሮ ሃላፊ ያነጋገረችው ሂሩት መለሰ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች ።ለተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት ክፍት መቀመጫዎች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ትናንት በተካሄደ ምርጫ ከአፍሪቃ ከእስያ ና ከላቲን አሜሪካ ቡድን በሰብአዊ መብት ጥሰት በሚከሰሱ አገራት ጭምር መያዛቸው እያነጋገረ ነው ። የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች በአብዛኛዎቹ ክፍለ አለማት ቡድኖች አስቀደሞ የተወሰነና የተዘጋጀ የሚሉትን የምርጫ ስርዓት አውግዘዋል ። የሰብአዪዊ መብት ተሟጋቹ የሂዩመን ራይትስ ዋች ይህ አይነቱ አሰራር እንዲስተካከል አሳስቧል ። የጂኔቫ ቢሮ ሃላፊ ጁሊ ደ ሪቬሮ የነዚህ ቡድኖች የምርጫው ሂደት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤን መስፈርት ይፃረራል ይላሉ ። « የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ለተመድ የሰብአዊ መብት ምክር ቤት አባልነት ምርጥ የሚባለውን ተወዳዳሪ መምረጥ ይኖርበታል ። ምክር ቤቱ ሲመሰረት የአባላት መመዘኛ ምርጥ የምክር ቤት አባላት በሰብአዊ መብት ምክር ቤት ውስጥ እንዲወከሉ ማድረግ ነው ። ይሁንና እንዳለ መታደል ሆኖ በአፍሪቃ በላቲን አሜሪካ በምሥራቅ አውሮፓና በእስያ የተወዳዳሪዎቹና የክፍት ቦታዎቹ ቁጥር እኩል ነበር ። ያ ማለት እጩ ሆነው የቀረቡት ሃገራት እንደሚመረጡ እርግጠኛ ነበሩ ። በዚህ የተነሳም ፉክክር አልተካሄደም ምርጫም አልነበረም ።

A general view during the opening session of the 5th UN Human Rights Council at the United Nations in Geneva, Switzerland, Tuesday, June 11, 2007. EPA/SANDRO CAMPARDO +++(c) dpa - Report+++
ምስል picture-alliance/ dpa
Delegates arrive at the assembly hall for the Human Rights Council special session on Sri Lanka at the European headquarters of the United Nations (UN) in Geneva, Switzerland, 26 May 2009. The meeting comes following UN Secretary-General Ban Ki-moon's visit to Sri Lanka on 22 and 23 May. EPA/SALVATORE DI NOLFI +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture-alliance/ dpa

በአፍሪቃው ቡድን በተካሄደ ምርጫ አይቮሪ ኮስት ኢትዮጵያ ጋቦን ኬናያና ሲራልዮን ያለተፎካካሪ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት መቀመጫዎች አግኝተዋል ። ሂዩመን ራይትስ ዋች እንደሚለው በአፍሪቃው ቡድን በተካሄደው በልማዳዊው የዙር ሥርዓት ምርጫ ኢትዮጵያን የመሳሰሉ ድርጅቱ በሰብአዊ መብት ጥሰት የሚከሳቸው አገራት ለመመረጥ ያበቃቸው ፉክክር አለመኖሩ ነው ። ጁሊ ደሪቬሮ

« በርከት ያሉ ተወዳዳሪዎች መቅረብ አለባቸው ። ያ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰብአዊ መብት በተሻለ ሁኔታ ሰብአዊ መብትን የሚያከብሩትን ለመምረጥ ይቻላል ። በአሁኑ ሁኔታ ግን ያ አልነበረም ። እንደ ኢትዮጳያ ያለች ሲቪል ማህበራቷን የምትጨቁን ፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች በሰብአዊ መበቶች ላይ መሥራት በማይችሉበት ሃገር የሰብአዊ መብት ቢጨቆንም መቀመጫ ማግኘት ችላለች ። »

U.N. High Commissioner for Human Rights, South African Navanethem Pillay, delivers her statement during the Human Rights Council Special Session on the situation of the human rights situation in Libya at the European headquarters of the United Nations in Geneva, Switzerland, Friday, Feb. 25, 2011. Sign reads in French : UN High Commissioner for Human Rights. (AP Photo/Keystone/Martial Trezzini)
ምስል AP

ለዚህ መፍትሄው ጁሊ ደ ሪቬሮ እንደሚሉት በርከት ያሉ ሃገራትን በተወዳዳዳሪነት ማቅረብ ነው ። ለምሳሌ ከምዕራባውያኑ ሃገራት ቡድን 5 ሃገራት ለ3 መቀመጫ ተወዳድረው በምርጫው ዩናይትድ ስቴትስ ጀርመንና አየርላንድ ሲያሸንፉ ግሪክና ስዊድን መቀመጫ አላገኙም ። በሰብአዊ መብት ጥሰት ስማቸው የሚነሳ ሃገራት በሰብአዊ መብት ምክር ቤት ውስጥ መቀመጫ የመያዛቸውን አጋጣሚ በመጠቀም የሃገራቸውን የሰብአዊ መብት ይዞታ እንዲያሻሽሉ ኢትዮጵያን በምሳሌነት በማጥቀስ ግፊት ማድረግ እንደሚገባ  አሳስበዋል ።  

« ዋናው ቁም ነገር እዚህ ላይ አሁን መመረጣቸው የሰውን ልጅ መብት በከፍተኛ ደረጃ ያከብሩ ዘንድ የሚላኩበትን ሁኔታ ፈጥሯል ። እንደ ኢትዮጵያ ያለች ሃገር አሁን የምክር ቤት አባል ሆናለች ። ስለዚህ የሰብአዊ መብት ይዞታዋን ማሻሻል አለባት ። በምክር ቤቱ መቀመጫ መያዝ እንደሚገባት ማሳየት አለባት ። እኛም በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ የፀዳ እንዲሆን ክትትል ና ግፊት ማድረግ አለብን ። »

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ