1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አሰራር ሲፈተሽ

ዓርብ፣ ጥቅምት 26 2003

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ዛሬ የዩናይትድ ስቴትስን የሰብዓዊ መብት ይዞታ መርምሯል ።

https://p.dw.com/p/Pzp5
የጄኔቫው የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትምስል AP

በዚሁ ወቅትም አሜሪካን በውጭ እና በሀገር ውስጥ ትፈፅማቸዋለች ሰለተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ከአንዳንድ አባል ሀገራት በኩል ጠንከር ያሉ ትችቶች ተሰንዝረዋል ። በምክር ቤቱ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኤይሊን ቻምበርሌይን ዶናሆ የሰብዓዊ መብት አያያዛችን እንከን የለሽ ነው ብለን አናምን ብለዋል ። በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ዕምነት የዋሽንግተን አስተዳደር እነዚህን ትችቶች በገንቢነታቸው የሚቀበል ከሆነ ለሌሎች አገራት ማለፊያ አቅጣጫ የሚያስይዝ አርአያ ሊሆን ይችላል ። የዶቼቬለዋ ኡልሪከ ማስት ኪርሽኒንግ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ዛሬ የአሜሪካንን የሰብዓዊ መብት ይዞታን መመርመሩን መነሻ በማድረግ ስለ ምክር ቤቱ አሰራር ያቀረበችውን ዘገባ ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች ።

ኡልሪከ ማስት ኪርሽኒንግ

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ