1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰብዓዊ መብቶች ይዞታ በኢትዮጵያ

ዓርብ፣ መስከረም 21 2003

እዚህ ጀርመን የሚገኘዉ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ይዞታ እንዲስተካከል የሚሟገተዉ፤ የኢትዮጵያዉያን ማህበር፤ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት እየተረገጠ ነዉ፤

https://p.dw.com/p/PSMs
የጀርመን ምክር ቤትምስል AP

አለወንጀል በርካታ የፖለቲካ እስረኞች በየወህኒዉ ይማቅቃሉ፤ የጋዜጠኞች ቢሮ ተዘግቷል፤ አብዛኛዉ ሰዉም ተሰዷል፤ አንዲ ፓርቲ ብቻዉን በ99,6 በመቶ ተመረጥኩ ብሎ ግዛቱን አስፋፍቷል ሲል አመለከተ። ማኅበሩ ትናንት በጀርመን ምክር ቤት የሰብዓዊ መብትን ጉዳይ ከሚከታተለዉ ኮሚቴ ጋ በመገናኘትም ጉዳዩን አብራርቷል። ከማኅበሩ በተጨማሪ በርሊን ተገኝተዉ የአገሪቱን የፖለቲካ ይዞታ ለምክር ቤቱ ካስረዱት መካከል በሌለሁነት የሞት ፍርድ ተፈረደብኝ ያሉትር ዶክተር ብርሃኑ ነጋ፤ እንዲሁም ዶክተር አረጋዊ በርሄና የቀድሞ ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻም ይገኙበታል።

ይልማ ኃይለሚካኤል ፤ ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ