1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰንደቅ ጋዜጣ እና የስም ማጥፋት ክስ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 13 2005

የሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ከሰባት ወራት በላይ ባስቆጠረ ዘገባ በፖሊስ ተይዞ መጠየቁንና በገንዘብ ዋስትና ከእስር መለቀቁን አመለከተ።

https://p.dw.com/p/18bhZ
ምስል DW

ጋዜጠኛ ፍሬዉ አበበ እንደገለፀዉ የፖሊስ ጥያቄ ያተኮረዉ ከወራት በፊት የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት ቤተመንግስቱን ለመልቀቅ እንዳልተዘጋጁና አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም ከቀድሞ መኖሪያ ቤታቸዉ እየተመላለሱ ለመስራት መገደዳቸዉ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳስከተለ በሚገልፀዉ ዘገባዉ ላይ ነዉ። የዜና ምንጩን መጠየቁን ያመለከተዉ የሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ከቀረበለት የስም ማጥፋት ክስ ተነስቶ ከሳሹ የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ከመገመት በቀር በትክክል የከሳሹ ማንነት እንዳልተገለፀለት አስረድቷል። ጋዜጠኛ ፍሬዉ አበበን ሸዋዬ ለገሠ አነጋግራዋለች። ባለፈዉ ሳምንት ስለሆነዉ ድርጊት በማብራራት ይጀምራል።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ