1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰዎች ለሰዎች ድርጅት መሪ ምላሽ

ሐሙስ፣ የካቲት 7 2005

«ሰዎች ለሰዎች» በሚል ስም የሚታወቀው ግብረ ሰናይ ድርጅት ሰሞኑን በግልጽልነት ጉድለት ገንዘብን በማባከን ተወቅሷል። ድርጅቱን በዋናነት የሚደግፉ ሁለት ለጋሾች ድጋፋቸውን እንደሚያቋርጡ ተናግረዋል። አሁን ድርጅቱን የሚመሩት ወይዘሮ አልማዝ በም ግን ከዶይቼ ቬሌ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ወቀሳውን አጣጥለውታል።

https://p.dw.com/p/17eGa
ምስል Solomon Mengist

እአአ በ1981 የመጀመሪያ ሥራውን በኢትዮጵያ የጀመረው ሰዎች ለሰዎች ግብረ ሰናይ ድርጅት በኢትዮጵያ በብዙ ስፍራዎች ብዙ ትምህርት ቤቶችን፣ የጤና ጣቢያዎችን እንዲሁም ሆስፒታሎችን ሰርቷል አሊያም አድሷል። በአገልግሎቱም ስመ-ጥር ድርጅት ሆኗል። ሰሞኑን በተለይም በጀርመን ጋዜጦች የወጡ ዜናዎች እንደሚያሳዩት ግን ድርጅቱ የአሰራር ግልጽነት እንደሚጎለው ለድርጅቱ የሚያበረከት የእርዳታ ገንዘብ እንደሚባክን ተነግሯል።አሁን ድርጅቱን የሚመሩት ወይዘሮ አልማዝ ግን ክሱን ጣጥለውታል።

በግልጽነት መጉደልና ገንዘብ አለአግባብ ተጠቅሟል በሚል ትችት የሰዎች ለሰዎች ሁለት ለጋሾች ድጋፋቸውን እንደሚያቋርጡ ተናግረዋል። ለድጋፉ መቋረጥ ምክንያት ነው ያሉት፤ ሰዎች ለሰዎች ድርጅቱ ትምህርት ቤቶችንና ሌሎች የህዝብ መገልገያ ተቋማትን ግንባታ ሲያጠናቅቅ፤ በኋላ ለመንግስት ያሰረክባል ሲሉ ይከሳሉ። ድርጅቱ መልሶ ስለማይቆጣጠራቸውም ትምህርት ቤቶቹ ወይም የጤና ማዕከላቱ ይፈራርሳሉ። ወይዘሮ አልማዝ ግን ይህ ኪስ መሰረት የለውም ሲሉ በግላቸውም እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።

በጀርመን የእርዳታ ድርጅቶችን የአሰራር ግልጽነት መርምሮ ማረጋገጫ የሚሰጥ ZENTRALINSTITUTES FUER SOZIALE FRAGE የተሰኘው ድርጅት፤ የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ግልጽ በሆነ አሰራራቸው ከሚታወቁት የእርዳታ ድርጅቶች አንዱ ነው ብሎ መናገሩን የጀርመን የዜና አውታር DPA ድርጅቱን ጠቅሶ ዘግቧል። ለሁለቱ ለጋሶች ድጋፋቸውን መከልከል ምክንያት የሆነው ሌላው ወቀሳ በአዲስ አበባ ሊሰራ የታቀደው የሰዎች ለሰዎች ጽህፈት ቤት ወጪ የተጋነነ ነው መባሉ ነው፣ ከጀርመኗ መርሐዊተ መንግት ጽህፈት ቤትም እንደሚበልጥ ተነግሯል። ወይዘሮ አልማዝ ለዚህ መልስ ሲሰጡ፣

ድርጅቱን እንደማይረዱ ካሳወቁ ሁለት ዋና ለጋሶች ጋር ወይዘሮ አልማዝ መነጋገራቸውንና፣ ከሁለቱ ግን አንደኛው ሊያነጋግራቸው ፈቃደኛ እንዳልሆነ ተናግረዋል። በበኩላቸው ግን ወይዘሮ አልማዝ ክሱን በህጋ እንደሚያጣሩ ገልጸዋል።

25 Jahre Menschen für Menschen
ምስል picture-alliance / dpa/dpaweb

ገመቹ በቀለ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ