1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰዎች ለሰዎች ድርጅት እቅድ

ሰኞ፣ ሰኔ 16 2006

ሰዎች ለሰዎች በኢትዮጵያ የሚያከናውናቸውን ሥራዎች በሙያዊ ተጠያቂነትና በግልፅነት እንዲሁም በመረጃ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለመሥራት አቅዷል።

https://p.dw.com/p/1COZI
Schauspieler Karl-Heinz Böhm mit Frau in Äthiopien
ምስል picture-alliance/dpa

ሰዎች ለሰዎችየተባለው ግብረ ሰናይ ድርጅት መዋቅሩን አጠናክሮ በኢትዮጵያ የጀመራቸውን ፕሮጀክቶች እንደሚቀጥል አስታወቀ ። በድርጅቱ በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ፕሮጀክቶች የበላይ ሃላፊና የጀርመን ፋውንዴሽን የስራ አመራር ቦርድ አባል ፒተር ሬነር ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ድርጅቱ በኢትዮጵያ የሚያከናውናቸውን ሥራዎች በሙያዊ ተጠያቂነትና በግልፅነት እንዲሁም በመረጃ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለመሥራት ማቀዱን ተናግረዋል። በቅርቡ ካረፉት ከድርጅቱ መሥራችና ከባለቤታቸው ከካርል ሃይንዝ በም እጎአ በ2011 «ከሶስት ዓመት በፊት» የድርጅቱን መሪነት የተረከቡት ወይዘሮ አልምዝ በም የሰዎች ለሰዎች የበላይ ጠባቂ ሆነው እንደሚያገለግሉም ሬነር አስታውቀዋል ። ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ