1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሲዳማ አካባቢ ምርጫና የተቃዋሚዉ ፓርቲ

ሐሙስ፣ መጋቢት 23 2002

ስምንት የፖለቲካ ማሕበራትን የሚያስተናብረዉ ጥምረት ከምርጫዉ የተሠረዘዉ ሥለእጩ አመዘጋገብ የፓርቲዉ መሪዎች ርስበርስ በፈጠሩት አተካራ ነዉ።በሲዳማ የሚንቀሳቀሱ የፓርቲዉ አባላትም የበላይ ሐላፊዎቻቸዉን ተጠያቂ አድርገዋል

https://p.dw.com/p/Ml2O
የ1997ቱ ምርጫምስል AP

የኢትዮጵያ መንግሥት ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ የዲሞክራሲና የአንድነት መድረክ በደቡብ ኢትዮጵያ በሲዳማ አካባቢ በሚደረገዉ ምርጫ እንዳይስታፍ መሰረዙን የአካባቢዉ ምርጫ ቦርድ ፅሕፈት ቤት አስታወቀ።ስምንት የፖለቲካ ማሕበራትን የሚያስተናብረዉ ጥምረት ከምርጫዉ የተሠረዘዉ ሥለእጩ አመዘጋገብ የፓርቲዉ መሪዎች ርስበርስ በፈጠሩት አተካራ ነዉ።በሲዳማ የሚንቀሳቀሱ የፓርቲዉ አባላትም የበላይ ሐላፊዎቻቸዉን ተጠያቂ አድርገዋል።ሥለ ምርጫ ዘመቻዉ ለመዘገበዉ ወደ አካባቢዉ የተንቀሳቀሰዉ ዩሐንስ ገብረ-እግዚአብሔር ከአዋሳ የላከልን ዘገባ አለ።

ዩሐንስ ገብረ-እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ