1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሳካሮቭ ሽልማት ለአንግ ሳን ሱቺ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 13 2006

ታዋቂዋ የበርማ የዴሞክራሲ ታጋይና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አንግ ሳን ሱቺ ሽትራስቡርግ በሚገኘዉ የአዉሮጳ ፓርላማ በመገኘት ትናንት የሰብዓዊ መብት የሳካሮቭ ሽልማት ተቀብለዋል።

https://p.dw.com/p/1A59o
ምስል Reuters

ሽልማቱ ለዴሞክራሲ ታጋይዋ እንዲሰጥ የተወሰነዉ የዛሬ 23ዓመት ነበር። ሱቺ በበርማ ማለትም ማይንማር ሰፍኖ የቆየዉን ወታደራዊ አገዛዝ ለበርካታ ዓመታት በሰላማዊ መንገድ በመታገልና ለሕግ የበላይነት መከበር በጽናት በመቆም በዓለም ዙሪያ እዉቅና አትርፈዋል። ለ15ዓመታት በቁም እስር የቆዩት አንግ ሳን ሱቺ በጎርጎሪዮሳዊዉ 1991ዓ,ም የሰላም የኖቤል ተሸላሚ ናቸዉ ። ሽልማታቸዉን ሲቀበሉ ባደረጉት ንግግርም የዴሞክራሲ ሂደት በሀገራቸዉ እንዲጠናከር የኅብረቱ ድጋፍ እንዳይቋረጥ አሳስበዋል። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሤ ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ