1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሳካሮቭ ተሸላሚው የኮንጎ ተወላጅ፣ የጋዜጦች አምድ፣...

ቅዳሜ፣ ኅዳር 20 2007

የዛሬው ትኩረት በአፍሪቃ ዝግጅት አፍሪቃ ውስጥ በወታደሮች እና በአማፂያን ስለሚደፈሩ ሴቶች የሚቃኝ ነው። የጋዜጦች አምድ ግጭት በሊቢያ፣ የማዳጋስካር ተስቦ፣ አምባገነን መሪዎች እና ባለቤቶቻቸው በአፍሪቃ የተሰኙ እና ሌሎች ዘገባዎችንም አካቷል።

https://p.dw.com/p/1Dx8P

አፍሪቃ ውስጥ በታጠቁ አማፂያን እና ወታደሮች የመደፈር ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶች በደልን አስመልክቶ ባከናወኑት ምግባር የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተወላጁ ዴኒስ ሙክዌጌ የ2014 የሳካሮቭ ተሸላሚ ለመሆን በቅተዋል። ዴኒስ ሙክዌጌ ማክሰኞ ኅዳር 17 ቀን፣ 2007 ዓም የአውሮጳ ምክር ቤት በመገኘት ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።