1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሳኻሮብ ሽልማት ፣

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 4 2004

በዐረቡ ዓለም ፤ አምና ስለተቀሰቀሰው የዴሞክራሲ ጥያቄና የለውጥ ትግል፣ በየጊዜው፤ እስካሁን ብዙ በመጻፍ ላይ ነው። የህዝብ ሰፊ አመጽ፤ ረጅም ጊዜ በሥልጣን ላይ የቆዩ አምባገነን መሪዎች እንዲገረሰሱ አድርጓል። አንዳንዶቹን እጅግ ንጧል።

https://p.dw.com/p/13Sp8
ተሸላሚዎችምስል picture-alliance/dpa

በሊቢያ የለየለት ጦርነት ነበረ ያስከተለው። ለውጥ ካስገኘው ከህዝባዊው  ንቅናቄ በስተጀርባ፤ አንዳንድ ለውጥ እንዲቀሰቀስ ያደረጉ አንዳንድ ግለሰቦች መወሳታቸው አልቀረም።  ከእነዚህም መካከል 5 ቱ በዛሬው ዕለት እሽትራስቡርኽ ውስጥ በአውሮፓ ፓርላማ የሳኻሮቭ ሽልማት  ተሰጥቶአቸዋል። በዚህ   ርእሰ-ጉዳይ ላይ  እሽቴፋኒ ዱክሽታይን ያቀረበችውን ዘገባ ተክሌ የኋላ እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።

የአውሮፓ ፓርላማ  ፕሬዚዳንት የርዚ ቡዜክ ፤ ባለፈው ጥቅምት ፤ የዘንድሮዎቹን የሳኻሮቭ ሽልማት አሸናፊዎች ሲያስታውቁ ልዩ ስሜት እንዳሳደረባቸው በድምጻቸው ይታወቅ ነበር።

1,«የአውሮፓ ፓርላማ የዘንድሮውን ለመንፈስ ነጻነት ፤የሳኻሮብን   ሽልማት ፣ ለ 5 የዐረቡ ዓለም የጸደይ ወቅት ተወካዮች ያቀርባል። እነርሱም ፣ ማቹ ቱኒሲያዊው ሙሐመድ ቡዓዚዚ፣ አስማ ማህፉዝ ከግብፅ፤ አህመድ ኧል ሱቤይር አህመድ ኧል ሳኑሲ ከሊቢያ፤ ራሳን ሳይቱኔ እንዲሁም አሊ ፋርሳት ከሶሪያ!ናቸው!» ሶሪያ ውስጥ በህቡዕ መንቀሳቀስ የጀመረችው ለሴቶች መብት የምትታገለው ራሳን ሳይቱኔህና በስደት የሚኖረው የአገሯ ሰው ሌላው ሶሪያዊ የካርቱን ሰዓሊ  አሊ ፋርሳት፤ ሁለቱም ፤ በዛሬው የሽልማት አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ላይ ሊገኙ አልቻሉም።  የተገኙት ግብጻዊቷ አስማ ማህፉዝና፤ በጋዳፊ የአገዛዝ አመን የፖለቲካ አፈንጋጭ  በመሆናቸው 31 ዓመት በእሥራት ያሳለፉት የ 77 ዓመቱ ሊቢያዊ  አዛውንት አህመድ ኧል ሱቤይር አህመድ ኧል  ሳኑሲ ናቸው። 

ቱኒሲያዊው የፍራፍሬና  አትክልት ነጋዴ  ሞሐመድ ቡዓዚዚ፣ ገና የ 26 ዓመት ወጣት ነበረ። ባለፈው ዓመት በታኅሳስ ወር፤ ፖሊሶች፤ እርሱን ጎሻሽመው  የሚሸጠውን ሸቀጣሸቀጥም  ቀምተው ከወሰዱበት በኋላ፤ ማዘጋጃ ቤት ፊት ለፊት በራሱ ላይ ቤንዚን አርክፍክፎ ራሱን ማቃጠሉ ይታወሳል። መገፋትን ፤ በደልን ፤ ድኅነትን ከእንግዲህ  በቃ! ሥራ አጥነት አከተመ! እያለም ሳይጮህ አልቀረም ነበር።

2,ድምፅ(የተቃውሞ)---------------------

በ2ኛው ሳምንትም ሞሀመድ ቡዓዚዚ ሀኪም ቤት ውስጥ፣ ህይወቱ አለፈች። ይሁን እንጂ ራሱን አቃጥሎ ህይወቱን ማሳለፉ፤ በመላይቱ ቱኒሲያ የተቃውሞ ማዕበል ቀሰቀሰ። በቱኒሲያ ብቻ ሳይሆን የተቃውሞው ማዕበል ወደ ሌሎቹ የዐረብ ሃገራት ተሸጋገረ።

3, የቪዲዮ መልእክት በ አስማ ማህፉዝ--------

እ ጎ አ ጥር 18 ቀን 2011 ፤ አንዲት ወጣት ሴት፤ በአንድ የኢንተርኔት ካሜራ፤ የግብፅ ገዥዎች አያያዝ እንዳንገሸገሻት ለተመልካቾች ገለጠች።

«ሙስና በቃ! ይህን አገዛዝ በቃ! እላለሁ። አለች። አስማ ማህፉዝ የ 26 ዓመት ወጣት ናት። የቀረጸችውን የቪዲዮ ፊልም፤ በ «ፌስቡክ» ዓምድዋ ላይ እንዲታይ ለቀቀችው። ተማጽኖ በማከል! ወደ ታህሪር አደባባይ ብቅ በሉና ፤ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንነሣ! መብታችሁ እንዲከበር ጠይቁ! ልባዊ የሆነውን የነጻነት ጥሪዋን  የተገነዘቡ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ግብጻውያን ተቀበሉላት። ማኅበራዊ ፍትኅ ፣ መሠረታዊ መብት፤ የዴሞካራሲ ተኃድሶ ለውጥ፤  ያቀረበቻቸው ጥያቄዎች ነበሩ። በአሁኑ ጊዜ አስማ ማኅፉዝ 14,000 ገደማ የፌስቡክ ደንበኞች ወይም ወዳጆች አሏት።

ራዛን ዛይቱኔህ ፤ የሶሪያ የሰብአዊ መብት አያያዝ መረጃ በተሰኘው የኢንተርኔት ድረ ገጽዋ፣ የሶሪያ ባለሥልጣት እንዴት በረቀቀ እኩይ ተግባር የሰውን ልጅ መብት እንደሚረግጡ ፤ ስንቱን ሰው ደብዛውን እንዳጠፉ ስታጋልጥ  የቆየች ስትሆን፤ ፕሬዚዳንት በሺር  ኧል አሰድ ተይዘው ለዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መርማሪ ፍርድ ቤት  እንዲቀርቡ መጠየቋ ታውቋል።

ግብጻዊቷ አስማ ማህፉዝ ዛሬ ሽልማት ስትቀበል ባሰማችው ንግግር እንዲህ ነበር ያለች።

«ሽልማቱ፣ ደፋር ልጃገረድ ናት ብሎ ከበሬታ ሰጥቶኛል። ግን አይደለም። ከአኔ የላቁ ብዙ ደፋር ግብጻውያን አሉ። ሽልማቱ ይገባቸዋል። በዚህ አገር የምኖርና ከአነርሱ መካከል አንዷ በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል።»

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ