1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሳውዲ ዐረቢያ እና የምስራቅ አፍሪቃ የኤኮኖሚ መድረክ ውይይት

ሰኞ፣ ኅዳር 7 2002

ሳውዲ ዐረቢያ እና የሳውዲ ዐረቢያ ባለሀብቶች ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪቃ ሀገሮች ገንዘባቸውን በግብር እና በሌሎች መስኮች ለማሰራት ፍላጎት እንዳላቸው የሳውዲ ዐረቢያ የንግድ እና የኢንዱስትሪ ሚንስትር ዶክተር አብደላ ቢን አህመድ ዛይናል እና የገንዘብ ሚንስትር ዶክተር ኢብራሂም አል ሳፋህ አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/KYFg
ምስል picture-alliance/ dpa

ሚንስትሮቹ ይህን የገለጹት የሳውዲ ዐረቢያ እና የሰባት የምስራቅ አፍሪቃ ሀገሮች የንግድና የኤኮኖሚ ምክክር መድረክ አዲስ አበባ ላይ ሲከፈት ባደረጉት ንግግር ነው። ከምክክሩ ጎን ከአንድ መቶ የሚበልጡ የሳውዲ ኩባንያዎች የተሳተፉበት የንግድ ትርዒት በአዲስ አበባ የሚሌንየም አዳራሽ ባለፈው ቅዳሜ ተከፍቶዋል።

ታደሰ እንግዳው/አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ