1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሪያድ ካርጎ ምሬት 

ሐሙስ፣ ነሐሴ 11 2009

በሳዑዲ ዓረቢያ ርዕሰ መዲና ሪያድ  ብቻ በሚሊዮኖች  ሪያል የሚተመን የኢትዮጵያዊያን ተመላሾች ንብረት በ ወኪል አስተላላፊዎች እጅ ይገኛል። ንብረቱ የኢትዮጵያ መንግስት ህገወጥ ተብለው ከሳዑዲ ዓረቢያ ለሚመለሱ ዜጎቹ በሰጠው የቀረጥ ነጻ መብት መሰረት በተመላሾቹ የተገዛ ነው።

https://p.dw.com/p/2iPW0
Äthiopien Rückkehrer
ምስል DW/S. Shiberu

ዋጋ የተከፈለበት የሳውዲ ተመላሾች ንብረት ዛሬም በመጋዘኖች ተከማችቶ ይገኛል።

ወደሀገር በአግባቡ ለማድረስ  በአደራ የተቀበሏቸውን የኤሌክትሮኒክስ ፣ የቤት ውስጥ መገልገያ እና አልባሳት በተገቢው መንገድ መላክ አለመቻላቸው ለሀሳብ ለጭንቀት እና ለተጨማሪ የማቆያ ኪራይ ወጪ እንደ ዳረጋቸው በሪያድ የሚገኙ ወኪል አስተላላፊዎቹ ይገልጻሉ። 

ስለሺ ሽብሩ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ