1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሳዑዲ አረቢያና የየመን አማፂን ዉጊያ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 14 2002

ሁቲ ተብሎ በሚጠራዉ የየመን የሺዓ ሐራጥቃ ሸማቂ ቡድን ላይ የየመንና የሳዑዲ አረቢያ መንግሥታት በጋራ የከፈቱት ጥቃት የአካባቢዉን የሐይል አሰላለፍ እየለወጠዉ ነዉ

https://p.dw.com/p/LCR6
የመን ድንበር-ሳዑዲ አረቢያ ተዋጊ ጄቶችምስል AP

የሳዑዲ አረቢያ ጦር ከየመን ሠርገዉ የገቡ ያላቸዉ የሺዓ አማፂያን ተቆጣጥረዉት የነበረዉን ግዛት ሙሉ በሙሉ ማስለቀቁን የሐገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።ሁቲ ተብሎ በሚጠራዉ የየመን የሺዓ ሐራጥቃ ሸማቂ ቡድን ላይ የየመንና የሳዑዲ አረቢያ መንግሥታት በጋራ የከፈቱት ጥቃት የአካባቢዉን የሐይል አሰላለፍ እየለወጠዉ ነዉ።ለወትሮዉ የማይጣጣሙት የመንና ሳዑዲ አረቢያ ኢራን ሸማቂዎቹን ታስታጥቃለች በማለት ይወነጅላሉ።ኢራን በበኩላ የሳዑዲ አረቢያን ርምጃ በየመን የዉስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ነዉ በማለት ተቃዉማዋለች።ነብዩ ሲራክ ዝር ዝሩን ከጂዳ ልኮልናል።

ነብዩ ሲራክ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ