1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

የሳዑዲ አረቢያ ግብር ኢትዮጵያዉያንን ጎዳ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 23 2009

መለስተኛ እና አነስተኛ ገቢ ያላቸዉ ኢትዮጵያዉያን ግብሩን መክፈል ሥላልቻሉ ገሚስ ቤተሰባቸዉን ወደ ኢትዮጵያ እየላኩ ነዉ

https://p.dw.com/p/2j2c6
Ethiopian International School Riyadh
ምስል DW/Sileshi Shibru

የሳዑዲ አረቢያ ግብር እና የኢትዮጵያዉይን ጉዳት

የሳዑዲ አረቢያ መንግስት በዉጪ ዜጎች ላይ የጣለዉ ወርሐዊ ግብር እዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንን ኑሮ እያወከዉ መሆኑ ተነገረ።መለስተኛ እና አነስተኛ ገቢ ያላቸዉ ኢትዮጵያዉያን ግብሩን መክፈል ሥላልቻሉ ገሚስ ቤተሰባቸዉን ወደ ኢትዮጵያ እየላኩ ነዉ።በዚሕም ምክንያት ሪያድና ጂዳ የሚገኙ የኢትዮያ ማሕበረሰብ ትምሕርት ቤቶች ለመማር ከሚመዘገብ ይልቅ መልቀቂያ ጠያቂዉ ተማሪ እየበረከተ ነዉ።የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ሐገሩ የሚኖሩ የዉጪ ዜጎች ካለፈዉ ሐምሌ ጀምሮ በነብስ ወከፍ በየወሩ መቶ ሪያል ግብር እንዲከፍሉ ደንግጓል።የሪያዱ ወኪላችን ስለሺ ሽብሩ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ስለሺ ሽብሩ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ