1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሴት ልጅ ግርዛት በአፋር

ሰኞ፣ የካቲት 2 2001

በኢትዮጵያ የሴት ልጅ ግርዛት ከቆየ ባህላዊ ልማድ ጋር በተያያዘ መልኩ በበርካታ አካባቢዎች የተለመደ ነው። ብዙዎች ይህን ጎጂ ባህል እንደየአካባቢያቸው ልማድና እምነት አንፃር ምክንያታዊ ለማድረግ ይጥራሉ።

https://p.dw.com/p/GqOG
ግርዛት በአፋር-ሀምቡርግ ሙዚየም
ግርዛት በአፋር-ሀምቡርግ ሙዚየምምስል AP
በምስራቅ አፍሪቃ ልዩ የባህል አምባ እንደሆነች የሚነገርላት ኢትዮጵያ፤ በበርካታ ጎጂ ልማዶችና ባህሎች ስትጠቃ ይስተዋላል። የሴት ልጅ ግርዛት በሀገሪቱ የዚሁ የጎጂ ባህል አንዱ ነፀብራቅ በመሆኑ፤ ሴቶች ብዙውን ግዜ ተጎጂዎች ናቸው። በተለይ ደግሞ የሴት ልጅ ግርዛት በከፋ ሁኔታ በሚከናወንበት የአፋር ክልል። የዛሬው ዝግጅታችን በአፋር ክልል የሴት ልጅ ግርዛት ከባህልና ከእምነት አንፃር ምን እንደምታ እንዳለው፣ የችግሩ ጥልቀት እስከምን እንደሚደርስ የሚያስቃኘን ይሆናል።