1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት ስርጭት

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 4 2005

በኢትዮጵያ የተንቀሳቃሽ ስልክ ማለትም ሞባይል ተጠቃሚዎች ቁጥር 18 ሚሊዮን መድረሱ ባለፈው ሰኞ በአዲስ አበባ በተጀመረው ሁለተኛው የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ጉባኤ ላይ ተገልጿል። ከሶስት ሚሊዮን የሚበልጡ ተጠቃሚዎች ደግሞ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው የኢንተርነት አገልግሎት ያገኛሉ።

https://p.dw.com/p/17262
ምስል DW/Brunsmann

የሀገሪቱ ሽቦ አልባ የኢንተርኔት ሽፋን ማደጉም ተነግሯል። አሁን አሁን በትላልቅ ከተሞች ብቻ ሳይሆን በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ተንቀሳቃሽ ስልክን መገልገል እንደ ቅንጦት መታየቱ የቀረ ይመስላል። ባለፈው ሰኞ በአዲስ አበባ በተጀመረው የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ የሥራ ፈጣሪነት ጉባኤ ላይ የተነገረውም ይህን በከፊሉ ያረጋገጠ ይመስላል።

Handy Afrika
ምስል Justin Sullivan/Getty Images For The Clinton Foundation

የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ገብረጺዮን ገብረሚካኤል እንዳሉት የሞባይል አገልግሎት ተጠቃሚዎች 18 ሚሊዮን ደርሰዋል። በሁለት ዓመት ውስጥ 45 ሚሊዮን የሞባይል ተጠቃሚዎች በኢትዮጵያ ይኖራሉ። ከሞባይል አገልግሎት መስፋፋት ጋር ተያይዞም የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር ከሶስት ሚሊዮን በላይ መድረሱን ሚንስትሩ አክለው ገልጸዋል።

ገመቹ በቀለ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ