1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስብርባሪ ብረታ-ብረት መጣያ የመሰለው ኅዋና፣ ወደፊት ሊያጋጥም የሚችለው አደጋ፣

ረቡዕ፣ መጋቢት 16 2001

ለዘመኑ የሳይንስና ሥነ-ቴክኒክ የምርምር ተቋማት፣ የጠፈር መንኮራኩር ማምጠቅ፣ ቀላል ነው። ችግሩ በሚላክ መንኮራኩር ሳቢያ ያልታሰበ ጣጣ እንዳያጋጥም፣ ከመከላከሉ ላይ ነው።

https://p.dw.com/p/HJWm
ከከባቢ አየር በላይ፣ ወደፊት ለምድራችን ጠንቅ የሚሆነው፣ ከጥቅም ውጭ የሆኑ የመንኮራኩሮች ስብርባሪ ብረታ-ብረት፣ምስል dpa

ሌሎች ዓለማትን ለማሰስ ስለሚመጥቁ መንኮራኩሮች ፣ ስልሚላኩ የኅዋ ቴሌስኮፖች፣ በየጊዜው እናወሳለን። ይህ ገና ተጨባጭ ውጤት ያልተገኘበትን ምርምር ይሆናል የሚመለከተው። ሌላው፣ የሰው ልጅ፣ ለዕለታዊ የተቀላጠፈ የስልክና የቴሌቭዥን አገልግሎት፣ ለተሽከርካሪዎችና መርከቦችም ጉዞና አቅጣጫ ማመላከቻ(Navigation) ልዩ መንኮራኩሮችም ሆኑ ሳቴላይቶችን የሚመለከት ሲሆን እስከቅርብ ጊዜ ጥቅሙ እንጂ ውሎ-አድሮ ከተጠቀሱት መሣሪያዎች ምን ዓይነት አደጋ ሊከሠት እንደሚችል እምብዛም አልተጤነበትም ነበር። ለመገናኛም ሆነ ለሌላ፤ ለስለላም ጭምር የሚመጥቁ ሳቴላይቶች ሲበላሹ ወይም ሲያረጁ ምን ይሆናሉ?

ተክሌ የኋላ፣

ሒሩት መለሰ፣