1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በካሌ አስከፊዉ የስደተኞች ሕይወት፤

ዓርብ፣ ሐምሌ 22 2008

ከፈረሳይ በስተሰሜን የምትገኘዉ የወደብ ከተማ ካሌ በድብቅ ወደእንግሊዝ ለመሻገር ከሚሞክሩ ስደተኞች ጋር በተያያዘ ስሟ ሲጠራ ሰነበተ። የድንበር ቁጥጥርና ፍተሻዉ በየጊዜዉ እየተጠናከረ ቢመጣም ወደዚች ከተማ የሚጎርፉ የስደተኞችን ቁጥር ግን አልቀነሰዉም።

https://p.dw.com/p/1JYbH
Flüchtlingscamps "Dschungel" in Calais
ምስል DW/H.T.Torode

[No title]

ከካሌ ከተማ የተወሰኑ ኪሌ ሜትሮች ወጣ ብሎ የሚገኘዉ የስደተኞቹ ጊዜያዊ መጠለያ ጫካ በአሁኑ ሰዓት ከ7 እስከ 8 ሺህ የሚገመቱትን ያስተናግዳል። ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት እንዲፈርስ የተደረገ ሲሆን በቅርቡም የከተማዉ አስተዳደር እንደሚያፈርሰዉ እየተነገረ ነዉ። ከዚህም ሌላ በስደተኞቹ መጠለያ ዙሪያ 4 ሜትር ርዝመት ያለዉ ግምብ ለማስገምባትም ዕቅድ መንደፉም ተሰምቷል። በፕላስቲክ ድንኳኖች እና በተለያዩ ቁሳቁሶች የተገነባዉ የስደተኞቹ መጠለያ መሠረታዊ ነገሮች ባይሟሉለትም የንግድ የእምነት ተቋማት እና ቤተ መጻሕፍትም ታክለዉበታል። ሰሞኑን ወደስፍራዉ ተጉዛ የነበረችዉ የፓሪሷ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ ተከታዩን ዘገባ ልካልናለች። ከዚህ ስፍራ በሌሊት ተነስተዉም በከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ በድብቅ በመጫን ወደሚመኟት እንግሊዝ ለመግባት ሲሞክሩም በርካቶቹ ሕይወታቸዉን በአሳዛኝ ሁኔታ አጥተዋል። በቅርቡ በዚህ ሁኔታ ያለፈችዉን ጨምሮ ካለፈዉ ጥር ወር አንስቶ በተመሳሳይ መንገድ ሕይወታቸዉ ያለፈ ስደተኞች ቁጥር ከስምንት እንደሚበልጥ ተሰምቷል። በሌላ በኩልም በስደተኞች መካከል በሚፈጠረዉ የእርስ በርስ ግጭት ሳቢያም ሕይወት እየጠፋ ይገኛል።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ