1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስደተኞች መከራ በፈረንሣይ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 7 2007

በፈረንሳይ የወደብ ከተማ፤ ካሌ የላስቲክ ድንኳ ቀልሰው የሚኖሩ ከኢትዮጵያና ኤርትራ ጭምር የመጡ ስደተኞች ብሪታንያ ለመግባት በሚያደርጉት አደገኛ ጉዞ በርካቶች ሕይወታቸውን እያጡ መሆኑ ተዘግቧል።

https://p.dw.com/p/1FyZa
Flüchtlinge in Calais
ምስል DW/H. Tiruneh

አብዛኛዎቹ ስደተኞች በሱዳን፣ በግብፅ እና በሊቢያ በረሃዎች መከራ የደረሰባቸው ናቸው። ከበረሃው ሀሩር አለያም ከአሸባሪዎች የሞት ጥላ ሸሽተው ፈረንሣይ የደረሱ እነዚህ ስደተኞች እዛው ፈረንሣይ ውስጥም ሌላ የሞት ጥላ እየተከተላቸው ነው። የዛሬው አውሮጳና ጀርመን ጥንቅር በፈረንሣይ የወደብ ከተማዋ ካሌ አድረገው ወደ ብሪታንያ ሲያቀኑ የሕይወት አደጋ ስለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን ይቃኛል። ኃይማኖት ጥሩነህ ስደተኞቹ አነስተኛ የላስቲክ ድንኳኖችን ጥለው ወደሰፈሩበት አካባቢ በማምራት የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅራለች።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አርያም ተክሌ