የስደተኞች ቁጥር ማሻቀብ
ረቡዕ፣ ሐምሌ 20 2003ማስታወቂያ
ቀጥሎ የምንጠራዉን ቁጥር መቀበል-የዶቸ ቬለዋ ሔለ የፕሰን እንደምትለዉ መቀበል ግር ያሰኝ ይሆናል።ግን እዉነት ነዉ።ከዓለም ሕዝብ 43 ሚሊዮኑ ስደተኛ ነዉ። ጦርነት፣ ሰዉሰራሽና የተፈጥሮ አደጋና፣ እና የመኖር ዋስትና እጦት ሕዝብን በብዛት ከሚያሰድዱ ምክንያቶቹ ዋነኞቹ ናቸዉ።እና ከየሶስቱ አንድ ሰዉ ሌላ አገር መሰደድን እንደ አማራጭ ያየዋል።በጣም ብዙዎች ደግሞ በየራሳቸው ሐገር ተፈናቃዮች ናቸው። አውሮጳ ባንፃሩ ድንበሯን እያጠበበች ነው። ሔለ የፕሰን ያሰባሰበችውን ልደት አበበ ታቀርበዋለች።
ሔለ የፕሰን
ልደት አበበ
ሒሩት መለሠ