1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የስጳኙ ሽብር

ዓርብ፣ ነሐሴ 12 2009

ፀጥታ አስከባሪዎች ከባርሴሎና 130 ኪሎ ሜርትር ርቀት ላይ በትገኝ ካምብሪልስ በተባለች የባሕር ዳርቻ ከተማ የሐሰት ቦምብ ያገለደሙ አምስት ሰዎችን ዛሬ ጠዋት ገድሏል።

https://p.dw.com/p/2iTlT
Barcelona Anteilnahme mit Opfern des Anschlags
ምስል picture alliance/ZUMAPRESS.com

(Q&A) Barcelona Terror-Reax - MP3-Stereo

 

ባርሴሎና-ስጳኝ ዉስጥ በርካታ ሰዎችን በመኪና ደፍጥጦ የገደለና ያቆሰለዉን ወጣት ለመያዝ የሐገሪቱ ፀጥታ አስከባሪዎች ሲያድኑ ነዉ የዋሉት።አደጋዉን ካደረሰዉ ጋር ተባብረዋል የተባሉ አራት ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል።ፀጥታ አስከባሪዎች ከባርሴሎና 130 ኪሎ ሜርትር ርቀት ላይ በትገኝ ካምብሪልስ በተባለች የባሕር ዳርቻ ከተማ የሐሰት ቦምብ ያገለደሙ አምስት ሰዎችን ዛሬ ጠዋት ገድሏል።በባርሴሎናዉ ጥቃት አስራ-አራት ሰዎች ተገድለዋል።ከአንድ መቶ በላይ ቆስለዋል።ሟች ቁስለኞቹ የ34 ዜጎች ናቸዉ።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴን ሥለ ጉዳዩ በሥልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ