1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስፖርት እና የባህል ትዕይንት በኑረንበርግ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 28 2003

በጀርመን በኑረንበርግ ከተማ የተካሄደዉ ዘጠነኛዉ የኢትዮጵያ የስፖርት እና የባህል ትዕይንት በአዉሮጳ እና በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዉያንን ማሰባሰቡ ተነገረ።

https://p.dw.com/p/Re7w
ኑረንበርግምስል DW

በእዚህ ለሶስት ቀናት በዘለቀዉ ትዕይንት ላይ በተለያዩ አዉሮጳ አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጽያዉያን የሚገኙበት ሃያ ሶስት የእግር ኳስ ቡድኖች ዉድድር አድርገዉ የዘንድሮዉን ግጥምያ ኢትዮ-ሆላንድ ኢትዮጽያዉያኑ የእግር ኳስ ቡድን ማሸኘፉ ተገልጾአል። በዝግጅቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በአሁኑ ወቅት በስዊትዘርላንድ ነዋሪ የሆኑት አትሌት መሃመድ ከዲር ነበሩ። ዘንድሮዉ ለዘጠነኛ ግዜ በኑረንበርግ የተካሄደዉ የኢትዮጽያዉያን መድረክ ከምንግዜዉም በላይ የተሳካለት እንደነበር፣ በቦታዉ የተገኙ እደምተኞች ገልጸዉልናል። በሌላ በኩል በኑረንበርግ ይህ የኢትዮጵያ የባህል እና የስፖርት ትዕይንት የተካሄደበት ቦታ በጀርመን በቱሪዝሙ ዘርፍ ተወዳጅ እና በርካታ የአለም አገራት ህዝብ የሚጎበኘዉ ቦታ መሆኑም ታዉቋል። ስለ ኑረንበርጉ የሶስት ቀናት የኢትዮጵያዉያን የስፖርት እና የባህል መድረክ መሰናዶ ይዘናል ያድምጡ!


አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ