1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስፖርት ዘገባ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 11 2003

በኢትዮጵያ የእግር ኳስ ታሪክ እንደ ንጉስ ይቆጠራል።

https://p.dw.com/p/Qgta
በስድስት የአፍሪቃ ዋንጫዎች ላይ የተሰለፈ
በስድስት የአፍሪቃ ዋንጫዎች ላይ የተሰለፈምስል AP

በተለይ አጠር ባለ ቁመቱ አየር ላይ ዘሎ በጭንቅላት ገጭቶ በሚያገባቸው ግቦቹ በርካታ አድናቂዎቹ ያስታውሱታል። መንግስቱ ወርቁ። ረቡዕ ታህሳስ 6 ቀን 2003ዓ,ም ለሰባ ዓመታት የኖረባትን ይህችን ዓለም ላይመለስባት ጥሏት ነጎደ። በስፖርት አዘዉታሪዎች በተለይም በእግር ኳስ አድናቂዎች ዘንድ ግን ለስሙ ህያዉነትን አላብሶ ትቶ አልፏል። እናም ስለኢትዮጵያ እግር ኳስ ከተነሳ መንግስቱ የጨዋታዉ ማድመቂያነቱ ይቀጥላል፤ ልክ ድሮ በአዲስ አበባ ስታዲዮምም ሆነ ጨዋታ በጀመረባቸዉ ሜዳዎች ድምቀትን ያላብስ እንደነበረዉ። እኛም ዛሬም ልናነሳዉ ወደድን፤ ከምንግዜም አድናቂዎቹና ደጋፊዎቹ መካከል፤ በተለምዶ አሸዋ ሜዳ ተብሎ በሚጠራው የአዲስ አበባው የራስ ሀይሉ ሜዳ ገና ድሮ ኳስ ሲጫወት ጀምሮ ከሚያዉቁት አንዱን፤ ወጣት የስፖርት ጋዜጣ አዘጋጅ፣ እንዲሁም ሌላ ወጣት የእግር ኳስ አሰልጣኝንም ጨምረን ስለ እግር ኳስ ኮከቡ መንግስቱ ወርቁ ከሚያዉቁትና ከሰሙት ጥቂቱን አካተን። ሳምንታዊዉ የስፖርት ዝግጅት ወቅታዊ የስፖርት ዜናዎችም አካቷል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሠ