1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያው የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት

ዓርብ፣ ኅዳር 25 2002

ሶሶት ሚኒስትሮችን ጨምሮ 19 ሰዎች የተገደሉበት ትናንት መቅዲሾ ውስጥ የደረሰው የአጥቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት ከአቅጣጫው እየተወገዘ ነው ።

https://p.dw.com/p/KqRe
ምስል AP

ጥቃቱ ካወገዙት ውስጥ የተበባሩት መንግስት ድርጅት የአውሮፓ ህብረት የአፍሪቃ ህብረት የአረብሊግ እንዲሁም ዩናይትድ ስቴትስ ይገኙበታል ። አዲሱ የሶማሊያ የሽግግር መንግስት ስልጣን ከያዘ ወዲህ በሀገሪቱ ከደረሱት ጥቃቶች ዓለም ዓቀፍ ትኩረት የሳበውን የትናንቱን አደጋ በሶማሊያ ተመሳሳይ ጥቃቶችን የሚያደርሰው አልሸባብ አልፈፀምኩም ሲል አስተባብሏል ። የግጭቶችን መንስኤ እና መፍትሄያቸውን የሚያጠናው የክራይስ ግሩፕ ባልደረባ ረሺድ አብዲ ለዶይቼቬለ በሰጡት አስተያየት ጥቃቱ አድራሹ አልሸባብ መሆኑ ግልፅ ነው ይላሉ ።

ሂሩት መለሰ /ሸዋዬ ለገሠ