1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያ ቀዉስና የኢጋድ ሥብሰባ

ረቡዕ፣ ግንቦት 12 2001

ለሶማሌዎች-በጣሙን ለመቅዲሾ ነዋሪዎች ግን ጥያቄዉ ዛሬን አድረን ነገ እንዉል ይሆን ወይ ሳይሆን አልቀረም።የድርድር ቀጠሮዉ-እስኪደርስ፥ የድጋፍ ቃሉ ገቢር እስኪሆን የሽግግር መንግሥቱ ባለበት መቆየቱም በይደር-የሚታይ ነዉ።

https://p.dw.com/p/HuIF
ፕሬዝዳንት ሸሪፍ ድጋፍ እስኪደርሳቸዉ በሥልጣን ይቆዩ ይሆን?ምስል AP

የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ-መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ አባል ሐገራት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ለሶማሊያ የሽግግር መንግሥት ድጋፍ ሥለሚሰጡበት ሁኔታ ለመነጋገር አዲስ አበባ ዉስጥ ተሰብስበዋል።ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ እንደዘገበዉ በዝግ ሲመክር ያረፈደዉን ስብሰባ የጠራችዉ ኢትዮጵያ ናት።

ታደሰ እንግዳዉ/ነጋሽ መሐመድ/ሂሩት መለሰ