1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያ ወንበዴዎችና የስዑዲ አረቢያ ቁጣ

ረቡዕ፣ ኅዳር 10 2001

«የወንበዴዎቹ እርምጃ ከአሸባሪነት ጥፋት እኩል የሚታይ ክፉ ደዌ ነዉ» ፋይስል

https://p.dw.com/p/Fy9m
አል ፈይሰል እና ብራዉንምስል picture-alliance/dpa

የሶማሊያ የባሕር ላይ ወንበዴዎች አንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ነዳጅ ዘይት የጫነት የስዑዲ አረቢያን ግዙፍ መርከብ ማገታቸዉ የሪያድ ልዑላንን ክፉኛ ነዉ ያስቆጣል።የሐገሪቱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ትናንት እንዳሉት የወንበዴዎቹ እርምጃ ከአሸባሪነት ጥፋት እኩል የሚታይ ክፉ ደዌ ነዉ።የባሕር ላይ ወንበዴዎቹን የሚያጠቃ በርካታ ዘመናይ አለም አቀፍ የባሕር ጦር ባካባቢዉ ሠፍሮ እገታዉ መቀጠሉ ዛሬም እንደትናንቱ ለብዙዎች እንቆቅልሽ ነዉ።ነብዩ ሲራክ ከጂዳ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።