1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያ የንግድ ጉባኤ በስቶክሆልም

ረቡዕ፣ ሰኔ 4 2006

ጉባኤው የስዊድንና የሶማሊያ መንግሥታዊና የግል ድርጅቶችን ለማገናኘት እንዲሁም ለስዊድናውያን ባለሃብቶች ስለ ሶማሊያ ተጨባጭ ሁኔታ ለማስረዳት ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑ ተመልክቷል ።

https://p.dw.com/p/1CGbZ
Stockholm Wirtschaftskonferenz Schweden Somalia ACHTUNG SCHLECHTE QUALITÄT
ምስል DW/T. Mehretu

በሶማሊያ ንግድና መዋዕለ ንዋይ ፍሰት ላይ ያተኮረ ጉባኤ ስዊድን ስቶክሆልም ውስጥ ትናንት ተካሄደ ። የስዊድን መንግስትና ቢዝነስ ስዊድን የተባለው ድርጅት በጋራ ያዘጋጁት ይኽው ጉባኤ የስዊድንና የሶማሊያ መንግሥታዊና የግል ድርጅቶችን ለማገናኘት እንዲሁም ለስዊድናውያን ባለሃብቶች ስለ ሶማሊያ ተጨባጭ ሁኔታ ለማስረዳት ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑ ተመልክቷል ። በጉባኤው ላይ ከስዊድንና ከሶማሊያ የተውጣጡ 150 ተሳታፊዎች ተገኝተዋል ። ጉባኤው የስዊድንና የሶማሊያ የንግድ ግንኙነት እንዲጠናከር አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ የስዊድን መንግሥት የንግድ ሚኒስትር ማስታወቃቸውን የስቶክሆልሙ ወኪላችን ቴዎድሮስ ምህረቱ ዘግቧል ።

ቴዎድሮስ ምህረቱ

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ