1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማልያ ፕሬዚደንትና የጠቅላይ ሚንስትራቸው ልዩነት

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 6 2001

በሶማልያ የሽግግር መንግስት ፕሬዚደንት አብዱላሂ ዩሱፍና በጠቅላይ ሚንስትራቸው ኑር ሀሰን ሁሴን መካከል ካለፉት ጊዚያት ወዲህ የቀጠለው ንትርክ እየተካረረ መጥቶ ፕሬዚደንቱ ትናንት ጠቅላይ ሚንስትራቸውን ማሰናበታቸውን ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/GGbQ
ፕሬዚደንት አብዱላሂ ዩሱፍ
ፕሬዚደንት አብዱላሂ ዩሱፍምስል AP

ጠቅላይ ሚንስትሩ ግን የፕሬዚደንቱ ውሳኔ ኢ ህገ መንግስታዊ ነው በሚል ውድቅ አድርገውታል። ፕሬዚደንት ዩሱፍ አንድ የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚንስትርን ሲያሰናብቱ ኑር ሀሰን ሁሴን ሁለተኛ ጊዜ መሆናቸው ነው። ኑር ሀሰን አንድ ዓመት በፊት የተሰናበቱትን አሊ መሀመድ ጌዲ ነበር የተኩት። የጀርመን የፖለቲካና የስነ ጥበብ ተቋም ተንታኝ ወይዘሮ አኔተ ቬበር ለዶይቸ ቬለ እንዳስረዱት፡ በፕሬዚደንቱና በጠቅላይ ሚንስትራቸው መካከል የቀጠለው ንትርክ በሶማልያ የሽግግር መንግስት ስራ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳርፎዋል።