1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶርያ ጊዜያዊ ሁኔታ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 12 2004

አስራ አምስት ወራት ያህል የዘለቀዉና ከአስር ሺህ በላይ ሰዎች የሞቱበት የሶርያ እንቅስቃሴ መቼና እንዴት ሊቋጭ እንደሚችል እስካሁን ሊታወቅ አልቻለም። የሰሜን አፍሪቃን ህዝባዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ የተነሳዉ የሶርያ ህዝባዊ አመፅ በፕሬዝደንት

https://p.dw.com/p/15Hxx
ምስል dapd

ባሽር አላሳድ አገዛዝ ላይ ያተኮረ እና ለዉጥ የሚሻ መሆኑ ቢታወቅም የፕሬዝደንት አሳድ መንግስት ግን እንደቱኒዚያ፤ ግብፅና አገዛዞች በቀላሉ የሚነቃነቅ አልሆነም። በቀድሞዉ የተመድ ዋና ፀሐፊ ኮፊ አናን የሚመራዉ የመንግስታቱ ድርጅትና የአረብ ሊግ የሶርያ ልዩ ልዑክ ያቀረበዉ የሰላም ሃሳብም ዉጤት ሊያመጣ እንዳልቻለና ሶርያም ወደከፋ የእርስበርስ ጦርነት ልትገባ እንደምትችል እራሳቸዉ ኮፊ አናን ለመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታዉ ምክር ቤት አስታዉቀዋል። የአዉሮጳ ጥናት ማዕከል የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም የሶርያን ሁኔታ የቃኘ ዉይይት አካሂዷል። ይህ በእንዲህ እንዳለለም የአዉሮጳ ኅብረት ሶርያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ለመጣል እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ