1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶሻል ዲሞክራቶች ፓርቲ የSPD 150ኛ አመት

ማክሰኞ፣ ግንቦት 13 2005

የጀርመን ሶሻል ዲሞክራቶች ፓርቲ በጀርመንኛው ምህፃር SPD ከነገ በስተያ 150 አመት ይደፍናል ። የዚህ አንጋፋው ፓርቲ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ምንድናቸው ? አርአያነቱ እስከምን ድረስ ነው ? ወዴትስ እያመራ ነው ። የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ።

https://p.dw.com/p/18bh4
05.2013 DW Highlights Mai 150 Jahre SPD
150 Jahre SPD Ferdinand Lassalle
የ SPD መሥራች ፈርዲናንድ ላዛለምስል AdsD der Friedrich-Ebert-Stiftung

በጀርመን የፖለቲካ ሂደት ለተገኙ መሠረታዊ ለውጦች ትልቅ አስተዋፅኦ በማበርከት ስሙ የሚነሳው የጀርመን ሶሻል ዲሞክራቶች ፓርቲ በጀርመንኛው ምህፃር የSPD ታሪክ የሚጀምረው ከ1860 ዎቹ መጀመሪያ ነው። የጀርመን አጠቃላይ የሠራተኛ ማህበር የተመሰረተበት በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ግንቦት23 1863 ለሰራተኛው ህዝብ መብት መከበርና ለፍትህ የሚታገለው የጀርመን ሶሻል ዲሞክራቶች ፓርቲ SPD ምሥረታ ቀን ተደርጎ ይወሰዳል ። መሥራቹም ፈርዲናንድ ላዛለ ሲሆኑየተመሰረተውም በዛክሰን ፌደራዊ ክፍለ ሃገር በምትገኘው በላይፕዚሽ ከተማ ነበር።6 አመት በኋላ ደግሞ አውጉስት ቤብልና ቪልሄልም ሊብክኔሽት የጀርመን ሶሻልዲሞክራት ሠራተኞች ፓርቲን መሰረቱ። አጠቃላዩ የጀርመን ሠራተኞች ማህበርና በኋላ የተመሰረተው የጀርመን ሶሻል ዲሞክራት ሠራተኞች ፓርቲ በ1875 ጎታ በተባለው ከተማ ተጣመሩ ። በዚህ መልኩ በሠራተኛ ማህበርነት ተነስቶ ወደ ፓርቲነትየተቀየረው የሶሻል ዲሞክራቶች ፓርቲ 3 አበይት መርሆች አሉት ። እነርሱም ነፃነት ፍትህና እኩልነት ናቸው ። ፍራንክፈርት ነዋሪ የሆኑት ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ የህግና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር የፓርቲውን ፍልስፋና ያብራሩልናል ።

እነዚህን ዋና ዋና መርሆች መመሪያውያደረገውየሶሻል ዲሞክራቶች ፓርቲ በ150 አመት ታሪኩ ከስኬት ጋር ውጣ ውረዶችም አልተለዩትም። በማናቸውም ፓርቲዎች ውስጥ የሚከሰቱትየሥልጣን ሽኩቻዎች ክፍፍልና የመርህ ለውጦች በየጊዜው ማጋጠሙ አልቀረም። ዶክተር ለማው ጣውረዶቹን ከአመሰራረቱ በመነሳትያስረዳሉ

የጀርመን አንጋፋፓርቲ SPD በጀርመን ማህበራዊ ፍትህ እንዲሰፍን ሃገሪቱም አሁን ለምትገኝበት የእድገት ደረጃ እንድትበቃ አስተዋፅኦ በማድረግ ስማቸው ከሚነሳው ፓርቲዎች አንዱ ነው። ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ ፓርቲውን በአርአያነትየሚያስነሱት ዐበይት ክንውኖች ይዘረዝራሉ።

Berlin/ Der ehemalige Bundesfinanzminister Peer Steinbrueck (SPD) spricht am Freitag (09.11.12) im Bundestag in Berlin. Nach monatelangem Hickhack will der Bundestag am Freitag das Betreuungsgeld beschliessen. Nach den Plaenen der Koalition soll es ab 1. August 2013 fuer Kinder zwischen ein und drei Jahren gezahlt werden, die von ihren Eltern nicht in eine oeffentlich gefoerderte Kindertagesbetreuung gegeben werden. Im kommenden Jahr sollen es zunaechst 100 Euro, ab 1. August 2014 dann 150 Euro sein. (zu dapd-Text) Foto: Michael Gottschalk/dapd
በመጪው ምርጫ የ SPD እጩ ተወዳዳሪ ፕየር ሽታይን ብሩክምስል dapd

ፓርቲው ጥሩ እንደሰራ ሁሉ በመጥፎም መነሳቱ አልቀረም ።ወደ ኃላ ሲገመገም በአባላቶቹ የተሳሳተ የፖለቲካአቅጣጫ የተሰሩ የፖለቲካ ስህተቶች ነበሩ። ዶክተር ለማ እነዚህን ስህተቶች በፓርቲው ደካማ ጎንነት አንስተዋል።

ከጀርመን ዋነኛዎቹ ፓርቲዎች አንዱ የሶሻል ዲሞክራቶች ፓርቲ SPD የፊታችን መስከረም በሚካሄደው በመጪው ምርጫ በተወዳዳሪነት ያቀረባቸው እጩ ፕየር ሽታይንብሩክ ምርጫውን ማሸነፍ መቻል አለመቻላቸውን ከወዲሁ መገመቱ ያዳግታል ። ፓርቲው 150 አመቱን ባከበረ ማግስት በለስ ቀንቷቸው ለድል ቢበቁ ባለፈው ሽንፈት የተበሳጩትን ደጋፊዎቻቸውን የሚክሱበት አጋጣሚ ሊሆን እንደሚችል ያታመናል ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ