1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶቺ የክረምት ኦሎምፒክስ ተጀመረ

ዓርብ፣ ጥር 30 2006

ዛሬ ማምሻዉን በተከፈተዉ በዓለም ዓቀፉ የክረምት ኦሎምፒክስ ከ87 ሃገራት የተዉጣጡ ከሁለት ሺህ ስምንት መቶ በላይ አትሌቶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

https://p.dw.com/p/1B4wS
Eröffnungsfeier Sotschi 07.02.2014
ምስል Getty Images/Damien Meyer

22ተኛዉ የክረምት ኦሎምፒክ በደቡባዊያ የሩስያ ከተማ ሶቺ ላይ በይፋ በድምቀት ተከፍቶአል። እስከ የካቲት 16 ቀን ድረስ በሚዘልቀዉ በዚሁ የክረምት ኦሎምፒክ ከ 87 የዓለም ሃገራት የተዉጣጡ 2900 ስፖርተኞች ለወርቅ፤ ለብር እና ለነሃስ ሜዳልያ እንደሚወዳደሩ ዘገባዎች,ቁመዋል። በሶቺዉ ኦሎምፒክ በ 98 የተለያዩ የስፖርት ዘርፎች ዉድድሩ እንደሚካሄድ ታዉቋል። በሶቺዉ የኦሎምፒክ ዉድድር ከጀርመን ብቻ 153 ስፖርተኞች ለመካፈል ቦታዉ ላይ ተገኝተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩኤስ አሜሪካ የስለላ ድርጅት፤ ሶቺ የክረምት ኦሎምፒክ የአሸባሪ ጥቃት እንዳይጣል ሲል ዳግም ትናንት ማስጠንቀቁዋ ይታወቃል። የክረምት ኦሎምፒክስ በሩስያ ሲካሄድ የዘንድሮዉ የመጀመርያ ሲሆን እንደ ፕሪዚዳንት ፑቲን የኦሎምፒክስ ዉድድሩ « ሩስያ ለዓለም ዘመናዊ ሆና በርዋን የምትከፍትበት መድረክ ነዉ»። በዚህም ዉድድሩ በከፍተኛ ጥበቃ እና ቁጥጥር ስር እንደሚሆን ፑቲን በተደጋጋሚ መናገራቸዉ ይታወቃል።

Sotschi 2014 Jamaika Bob 06.02.2014
ምስል Getty Images

የሩሲያዋ በረዷማ ግዛት ሶቺ ይህን ስፖርታዊ ዉድድር ለማስተናገድ ላለፉት ዓመታት ከፍተኛ መሰናዶ ስታደርግ ቆይታለች። ዘገባዎች እንደሚሉት ከዛሬ 7 ዓመት በፊት ሶቺ የተመለከተ ዛሬ ፍፁም አያዉቃትም፤ በዘመናዊና ዉድ የክረምት ስፖርት ማዘዉተሪያዎች ደምቃለች። የፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን አስተዳደር ሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ለምታስተናግደዉ ለሶቺዉ የክረምት ኦሎምፒክ ከፍተኛ ገንዘብ አዉጥቷል በሚል እየተተቸ ነዉ፤ 51 ቢሊዮን ዶላር። በመርሃግብሩ መሠረትም ዛሬ የሚከፈተዉ የክረምት ኦሎምፒክስ የካቲት አስራ ስድስት ያበቃል። የሎንደኗ ዘጋቢያችን ሃና ደምሴ ተከታዩን ዘገባ ልካልናለች

ሃና ደምሴ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ