1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሽብርተኝነት ተፅዕኖ በፈረንሳይ ኤኮኖሚ ላይ

ረቡዕ፣ ኅዳር 8 2008

በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ባለፈው ዓርብ የተጣለው የሽብር ጥቃት በሀገሪቱ ኤኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫና አሳደረ። ጥቃቱ በቱሪዝም እና በንግዱ ዘርፎች ላይ በቀላሉ የማይገመት ተፅዕኖ አሳርፎዋል ።

https://p.dw.com/p/1H8Ej
Frankreich Eiffelturm in Paris
ምስል picture-alliance/dpa/W. Grubitzsch

የሽብርተኝነት ተፅዕኖ በፈረንሳይ ኤኮኖሚ ላይ

በፈረንሳይ የሚኖረው ሐዝብ ሰላማዊ ኑሮ መምራት ይፈልጋል። ሀገሪቱን በመጎብኘት ላይ ያለዉ ቱሪስትም ሆነ በከተማዋ የሚዘዋወረዉ ሰላማዊ ሕዝብ ፀጥታዉን ይሻል። ከትንሹ ነጋዴ እስከ ትልቁ የንግድ ኩባንያ ባለቤት የሆነዉ ነጋዴም ቢሆን ንግዱ የሰመረ፣ የድካሙን ዋጋ በፀጥታ እና ደሕንነቱ በተጠበቀ መንገድ መሰብሰብን ይሻል። በዚህ መኃል ግን ሽብር ፈጣሪዎች ሳይታሰብ የሽብር ጥቃትን ሲጣል ግን የከተማዋ ጎብኝ ቱሪስቱም ሆነ ነዋሪዉ ኑሮዉ ሥራዉ ደሕንነቱ ሁሉ ይዘበራረቃል። ነጋዴዉም ቢሆን የሥራዉና የኑሮው መሠረት ይናጋል ይዳከማል። በዓመት ከሰማንያ ሚሊዮን ሰው በላይ የሚጎበኛት ፈረንሳይ በተለይ ከተማዋ ፓሪስ አሁን ያጋጠማት ችግርም ይኸው ነዉ። የቱሪዝሙ ዘርፍ በፈረንሳይ ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢ ላይ የያዘው ድርሻ በቀላሉ የሚገመት አይደለም። የፈረንሣይ አየር መንገድ ኤር ፍራንስ እና አኮርር የሚባለው የብዙ ሆቴሎች ባለንብረትእንዳረጋገጡት፣ በቅርቡ በተፈጠረው አደጋ -በጥቂት ቀናት ጊዜ ውስጥ ብቻ፣ የአክሲዮናቸው ዋጋ አሁን በጉልህ ቀንሶዋል።

Logo Air France
ምስል Air France

አንድርያስ ቤከር / ይልማ ኃይለሚካኤል

አዜብ ታደሰ