1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሽብርተኝነት ትግልና ልሉ የጦር መሳርያ ቁጥጥር ሕግ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 28 2008

ባለፈው ሳምንት በዩኤስ አሜሪካ ካሊፎርንያ ግዛት ሳንበርናዲኖ ከተማ የ14 ሰዎች ህይወት በቀጠፈውና 22 ሰዎችን ለጉዳት የዳረገው ጥቃት ከሸብርተኝነት ጋር እንደሚያያዝ መገለጹን ተከትሎ ዩኤስ አሜሪካ ሽብርተኝነትን ለመታገል የምታደርገው ጥረት በፖለቲከኞች ዘንድ አዲስ የክርክር ርእስ ከፍቷል።

https://p.dw.com/p/1HJMU
US-Präsident Barack Obama
ምስል picture-alliance/dpa

የሃገሪቱ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ህግም እያነጋገረ ነው። የፕሬዝዳንት ኦባማ አስተዳደር እየተከተለ ያለው በተዋጊ አውሮፕላኖች የአይሲስ ይዞታዎችን የመደብደብ ስትራቴጂ ውጤት ሊያመጣ አይችልም፣ አይሲስ ከሶርያና ኢራቅ አልፎ በአሜሪካና ሌሎች የምእራብ ሀገራት ላይ የሽብር ስጋት ደቅኗል የሚሉት የፕሬዝዳንት ኦባማ ተቃዋሚዎች የጸረ አይሲስ ዘመቻው በእግረኛ ወታደር ጭምር እንዲታገዝ የፈልጋሉ። የሶርያና ኢራቅ ስደተኞች ለጊዜው ወደአሜሪካ እንዳይገቡ እንዲከለከለም ይጠይቃሉ።

የፕሬዝዳንት ኦባማ አስተዳደር ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ ያለው ልል የጦር መሳሪያ ቁጥጥር በሃገር ውስጥ የሽብር ጥቃት ሊያደርሱ ለሚችሉ ሰዎች ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር በመሆኑ የቁጥጥር ህጉ መሻሻል ይኖርበታል ይላል።

ናትናኤል ወልዴ/ከዋሽንግተን ዲሲ

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ