1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀኝ አክራሪዎች ጥቃት 10ኛ ዓመት በኮሎኝ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 3 2006

በኮሎኝ ከአሥር ዓመት በፊት የቀኝ አክራሪዎች በብዛት የውጭ ሀገር ዜጎች፣ በተለይም ፣ ቱርካውያን በሚኖሩበት ሠፈር አንድ የሚስማር ቦምብ አፈንድተው ከ22 የሚበልጡ ሰዎች ሲያቆስሉ አንድም የሀገሪቱ ፖለቲከኛ ጥቃቱ ወደተጣለበት ቦታ

https://p.dw.com/p/1CFYh
ምስል picture-alliance/dpa

በመሄድ ተጎጂዎችን አላፀናናም። በዚያን ጊዜ ምርመራውን ያካሄዱት የፀጥታ ኃይላት ቦምቡን ያፈነዱት እርስ በርስ የሚፈላለጉ ቱርካውያን ናቸው በሚል ትኩረታቸውን በሰለባዎቹ ላይ በማሳረፋቸው ጥቃቱን የጣሉት ሳይያዙ ነበር የቀሩት፣ ጥቃቱ ራሱን የናሽናል ሶሻሊስት ሥውር ድርጅት፣ በምሕፃሩ «ኤን ኤስ ኡ» ብሎ የሚጠራው የቀኝ አክራሪዎች ቡድን አባላት መጣላቸው የኋላ ኋላ ሊታወቅ ችሎዋል። ትናንት የጥቃቱ አሥረኛ ዓመት ሲታሰብ የጀርመን ፕሬዚደንት ዮአኺም ጋውክ በኮሎኝ በመገኘት ለጥቃቱ ሰለባዎች የድጋፍ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

አንድሬያ ግሩናው/ይልማ ኃይለ ሚካኤል

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ