1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀድሞዉ ኦሮሚያ ፕሬዝዳንት ዜና ዕረፍት

ሐሙስ፣ የካቲት 27 2006

በ1993 የኢሕአዴግ ዋና መሠረት የሚባለዉ ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሐት) ለሁለት ሲገመስ ግን የአንጋፋዉ ፖለቲከኛ የኢሕአዴግነት ጀንበር ስታዘቀዝቅ-የወጣቱ ካድሬ የኢሕአዴግ የፖለቲከኛነት ጀምበር ባንፃሩ ደመቀች።አቶ አለማየሁ የያኔዉን ጠቅላይ ሚንስትር የአቶ መለስን ልዩ ትኩረት እና እንክብካቤም አገኙ።

https://p.dw.com/p/1BLPv
ምስል picture-alliance/dpa

የኦሮሚያ መስተዳድር ፕሬዝዳት እና የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዉ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሊቀመንበር የነበሩት አቶ አለማየሁ አቶምሳ አርፈዋል።አቶ አለማየሁ በጠና ታመዉ በሕክምና ሲረዱ ቆይተዉ ነዉ ያረፉት።አቶ አለማየሁ ኦሕዴድን በአባልነት የያዘዉ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በኦሕዴድ እና በኦሮሚያ መስተዳድር በተለያዩ የሥልጣን ደረጃዎች አገልግለዋል።በቅርቡ የሚያዉቋቸዉ እንደሚሉት የድርጅታቸዉን አላማ ለማሳካት አበክረዉ የሚታገሉ፥ ሙስናን እና በሥልጣን መበልፀግን አጥብቀዉ የሚቃወሙ ፖለቲከኛ ነበሩ።ነጋሽ መሐመድ አጭር ዘገባ አጠናቅሯል።


ምናልባት በወጣትነት እድሜቸዉ ከፍተኛ የሥልጣን እርከንን ከተቆናጠጡ ጥቂት የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት አንዱ ናቸዉ።ከእንግዲሕ ነበሩ-ነዉ የሚባሉት።አቶ አለማየሁ አቶምሳ። የቀድሞዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ደርግ ከመወገዱ ከአመት ከመንፈቅ ግድም በፊት ኦሕዴድ-ኢሐዴግን ተቀላቀሉ።1981።

ደርግ በ1983 ከሥልጣን ተወግዶ ኢሕአዴግ ሥልጣን ሲይዝ-በሃያዎቹ መጀመሪያ የእድሜ ክልል ዉስጥ ከሚገኙ የኦሕዴድ-ኢሕአዴግ ቀልጣፋ ካድሬዎች አንዱ ሆኑ።የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳትና የኦሕዴድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የተዋወቋቸዉ እንደ ፖለቲካ ጓድ የቀረቧቸዉም ያኔ ነበር።

አንጋፋዉ ፖለቲከኛ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳት ሲሆኑ፥የወጣቱ ካድሬ የቅርብ አለቃ-ሆነዉ በቅርብ ይሰሩ ገቡ።1987።ግንኙነታቸዉ የየዕለት፥ በጣም ከዘየገየ የየሳምንት ነበር።

ዶክተር ነጋሶ የያኔዉን ወጣት ካድሬ ታታታሪ፥ ቀልጠፋና ትጉሕነቱን ያስታዉሳሉ።በ1993 የኢሕአዴግ ዋና መሠረት የሚባለዉ ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሐት) ለሁለት ሲገመስ ግን የአንጋፋዉ ፖለቲከኛ የኢሕአዴግነት ጀንበር ስታዘቀዝቅ-የወጣቱ ካድሬ የኢሕአዴግ የፖለቲከኛነት ጀምበር ባንፃሩ ደመቀች።አቶ አለማየሁ የያኔዉን ጠቅላይ ሚንስትር የአቶ መለስን ልዩ ትኩረት እና እንክብካቤም አገኙ።

ቀስበቀስ ከመሠላሉ ጫፍ ደረሱ።በሁለት ሺሕ ሁለት የኦሕዴድን የሊቀመበርነት ሥልጣን ያዙ።ባመቱ ደግሞ ከኢትዮጵያ መስተዳድሮች ሁሉ በሕዝብ ብዛት፥ በቆዳ ሥፋት፥ በሐብትም የመጀመሪያዉን ሥፍራ የያዘዉን የኦሮሚያ መስተዳድርን ፕሬዝዳትነት ጠቀለሉ።

አቶ አለማየሁ በተለይ ሙስናንና ሙሰኞችን አጥብቀዉ የሚቃወሙ ፖለቲከኛ መሆናቸዉ ይነገርላቸዋል።ዶክተር ነጋሶም የሚነገረዉን ሰምተዋል።

አንዳዶች እንደሚሉት አቶ አለማየሁ ሙስናን አጥብቀዉ መቃወማቸዉ በፖለቲካ ጓዶቻቸዉ ዘንድ ቂም ሳየተርፍባቸዉ አልቀረም።አንዳንድ ወገኖች ደግሞ ከዚሕም አልፈዉ አቶ አለማየሁን ለሞት በዳረገዉ በሽታ የተለከፉት ተመርዘዉ ነዉ እስከማለት ይደርሳሉ።አንዱም በመረጃ አልተረጋገጠም። የተረጋገጠዉ፥-ቢሎ ቦሼ ወረዳ-ምሥራቅ ወለጋ በ1961 ተወለዱ።ከሁለት ሳምንት በፊት ሥልጣናቸዉን ለቀቁ።ባንኮክ-ታይላንድ ሲተከሙ ነበር።ሞቱ።የሰወስት ልጆች አባት ነበሩ።

Wahl in Oromia Äthiopien 23.Mai 2010
ምስል DW
Meles Zenawi Archivbild 1991
ምስል picture-alliance/dpa

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ