1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ታምራት ላይኔ ከእስር መለቀቅ፣

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 10 2001

ቀድሞ የኢትዮጵያ ጠ/ሚንስትርና የመከላከያ ሚንስትር የነበሩት አቶ ታምራት ላይኔ ከ 12 ዓመታት እስር በኋላ ዛሬ ተፈትተዋል። በ 1988 ዓ ም ፣ በተደራራቢ የሙስና ወንጀል ተከሰው፣ ለእሥራት የተዳረጉት አቶ ታምራት ፣ በ2 ክሶች ጥፋተኛ ተብለው 18 ዓመት ጽኑ እሥራት ተፈርዶባቸው ነበር።

https://p.dw.com/p/GJym
ምስል dpa

ያም ሆኖ፣ ታደሰ እንግዳው፣ ከአዲስ አበባ በላከው ዘገባ ላይ እንዳለው በሀገሪቱ ህግ ¾ኛውን የእሥር ዘመኑን በመልካም ሥነ-ምግባር ለፈጸመ፣ የሚሰጠው የአምክሮ ማህረት ታስቦላቸው ፣ ከ 12 ዓመት የእሥራት ጊዜ በኋላ ዛሬ ከእሥር ተለቀዋል