1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀድሞው የየመን ፕሬዚዳንትና የዩናይትድ ስቴትስ አተካራ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 27 2007

የቀድሞው የየመን ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳሌህ፣ ዩናይትድ ስቴትስ አገር ለቀህ ውጣ አልችኝ! ሲሉ ምሬት -አዘል ቃል ቢሰነዝሩም ዩናይትድ ስቴትስ ፣ ሳሌህ ያሉትን አለማድረጓን ገልጻለች። ባለፈው ሳምንት ዩናይትድ ስቴትስ፤

https://p.dw.com/p/1DiZO
Karte Jemen englisch

በሳሌህና ሁለት የሺዓ ሙስሊም ሁቲ ቡድን መሪዎች ላይ የዓለም አቀፍ ጉዞ እገዳ እንዲደረግ፤ በውጭ ያላቸው ማንኛውም ንብረትም እንዳይንቀሳቀስ ያደረግ ዘንድ ፤ የተባበሩትን መንግሥትት የፀጥታ ጥበቃ ም/ቤት ጠይቃ እንደነበረ የሚታወስ ነው። እገዳው ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ ሳይሆን እንደማይቀርም በመነገር ላይ ነው። ስለቀድሞው የየመን ፕሬዚዳንት ስሞታና ስለወቅታዊው የአገሪቱ ፖለቲካዊ ይዞታ በሰንዓ የሚገኘውን ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖትን በስልክ አነጋግሬው ነበር።

ግሩም ተ/ሃይማኖት

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ