በአሸባሪነት የተከሰሱ ተፈረደባቸው
ዓርብ፣ ሰኔ 16 2009ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አቃቤ ህግ በአሸባሪነት በከሰሳቸው በቀድሞ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ እና የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ አባላት ላይ ዛሬ ከ4 ዓመት ከ2 ወር እስከ 4 ዓመት ከስድስት ወር እሥራት በየነ። ችሎቱ የአረና ትግራይ ፓርቲ ሊቀመንበር አብርሐ ደስታ እና የቀድሞው የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ(አንድነት) ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል ዳንኤል ሺበሺን ጉዳይ ለመመልከት ተሰይሞ ነበር። ሆኖም ዳንኤል ሺበሺ የመከላከያ ምስክሮች ሲያቀርቡ አብርሃ ደስታ ግን ችሎቱ ላይ አልተገኙም። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ