1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀጠለዉ የሙስሊሞች እንቅስቃሴ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 28 2005

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች፣ የኢትዮጵያ መንግስት ሐይማኖታዊ ነፃነታችን ረግጦአል በማለት በየሳምንቱ ዓርብ የጁምዓ ፀሎትንና ሥግደትን ተከትሎ የሚያሰሙትን ተቃዉሞ ባለፈዉ አርብ ሚያዝያ 25 አላሰሙም ነበር።

https://p.dw.com/p/18TBf
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

ሙስሊሞቹ ተቃዉሞዉን ለአንድ ቀን ያቋረጡት ክርስትያኑ ኢትዮጵያዊ በዓሉን እንዲያከብር እንደሆነ አስታዉቀዋል። ድምጻችን ይሰማ በሚል መርህ ሙስሊሞች ዘወትር አርብ ከሚያደርጉት ጸሎት በኋላ የሚያሰሙትን ተቃዉሞ፤ የስቅለት በዓልን ምክንያት በማድረግ ያቋረጡት ፤ ክርስትያኑን እና ሙስሊሙን ለማጋጨት የሚፈልጉ ወገኖች አጋጣሚዉን እንዳይጠቀሙ በማሰብ እንደሆንም ገልጾአል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት ጥርጣሪ ካሰራቸዉ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች ሁለቱ ማለት ሙባረክ አደም እና ካሊድ ኢብራሂም የቀለበት ስነ-ስርአት ማካሄዳቸዉ ተነገረ። ስነ-ስርአቱ የተካሄደዉ በርካቶች በተገኙበት ቃሊቲ እስር ቤት በኬክ ቆረሳ ስነ-ስርአት እና ፤ በኋላም እስረኞቹ በሌሉበት በሆቴል የምሳ ግብዣ እንዲሁም ፤ ቄራ በሚገኘዉ መስጊድ በተደረገ የፀሎት ስነ-ስርዓት እንደሆነ ወኪላችን ዮሃንስ ገ/እግዚአብሄር ከአዲስ አበባ የላከልን ዘገባ ያሳያል።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ

Gefangenen Hochzeit in Äthiopien
ምስል DW/Y. Gebreegziabher
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ