1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀጠለው ተቃውሞ በኢትዮጵያ

Merga Yonas Bulaሰኞ፣ ነሐሴ 2 2008

ቅዳሜ እለት በኦሮሚያ ክልል በተካሄዱ ሰላማዊ ሰልፎች ላይ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ ከ30 በላይ ሰዎች መሞታቸዉ እንዲሁም በመቶች የሚቆጠሩ መታሰራቸው እየተዘገበ ነው። እሁድ በአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ ባህርዳር ከተማ ተመሰሳይ ሰላማዊ ሰልፍ በተካሄደበት ወቅት ከሰባት በላይ ሰዎች መሞታቸዉ እየተዘገበ ነው።

https://p.dw.com/p/1Jdk1
Äthiopien Protest
ምስል Reuters/T. Negeri

[No title]

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በኦሮሚያ ክልልና በባህርዳር ከተማ በተካሄደው ተቃውሞ እና ሰላማዊ ሰልፍ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ ብዙ ሰዉ መሞታቸዉ እና መታሰራቸዉ ኢየተዘገበ ነው። ቅዳሜ እለት አዲስ አበባና ድሬ ዳዋን ጨምሮ በመላ ኦሮምያ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፉ መነሻው ምክንያት የታሰሩት የፖለቲካ እስረኞች <<በአስሸኳይ>> እንዲፈቱ፣ በኦሮሚያ ዉስጥ የሚደረገዉ <<መጠነ ሰፊ ግድያ እንዲቆምና ገዳዮች ለፍርድ እንድቀርቡ>>፣ ኦሮሚያ ራሱን የማስተዳደር መብቱ እንድጠበቅለት እና የህዝቦች መብት እንዲከበር ለመጠየቅ መሆኑ ነው የተነገረው ። እሁድ እለት በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ላይ የተደረገዉ ደግሞ የወልቃይ ጠጌዴ ጉዳይ ላይ ያነጣጠረ ሆኖ በአገርቱ በተለያዩ ቦታዎች እየተካሄደ ባለዉ ተቃዉሞ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች በአግባቡ መልስ እንድያገኙ የሚል ነበር።


ስማቸዉ እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የአዳማ ከተማ ነዋሪ ከተማዋ ቅዳሜ እለት ከሁለት ሰዓት ጀምሮ ደራርቱ አደባባይ ህዝብ የተለያዩ መፍክሮችን ይዞ እንደወጣና ብዙ የፀጥታ አካላት እንደነበሩ ይናገራሉ። ይህ ድብደባና ከቤት ወደ ቤት ኢየሄዱ ማሰርም እሁድ እና ዛሬም እንደቀጠለ እኝ አስተያየት ሰጭ ይናገራሉ። ሌላኛዉ አስተያየት ሰጭ የባህር ዳር ነዋሪ መሆናቸዉን ጠቅሰው ትላንት ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም እንደተጀመረ ጠቅሰው በዋላ ላይ ወደ ግጭት ማምራቱን ያስረዳሉ።

ህዝቡና ታጣቂ ኃይሎች ዛሬም እንደተፋጠጡ መሆኑንም እኚሁ የከተማዋ ነዋሪ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።
ድምፅ ባህርዳር 2
የኢትዮጲያ መንግስት በኦሮምያ ሆነ በባህርዳር የተቃውሞ ሰልፎቹ ከመካሄዳቸው አስቀድሞ ከዓርብ ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር ተዘግቧል ። የኢንተርኔት አገልግሎት ዛሬ እንደገና ቢጀምርም ወደፊት ሙሉ በሙሉ ሊዘጋ ይችላል የሚል ፍራቻ በማህበረሰቡ ላይ ፈጥረዋል ትላለች የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነችው ኤዴን ጋሻዉ ።ለችግሩ እልባት ለመስጠት ይህ መፍትሄ አይሆንምም ትላለች።

በፌስቡክ ደረ-ገፃችን ላይ አስተያየታቸውን ከሰጡን መካከል ሰላማዊ ሰልፉን <<ፀረ/ሰላም>>፣ የአገሪቱን አንድነት የሚያደፈርስ ነዉ ስሉ አስተያየተቸዉን የሰነዘሩም አሉ። ሌሎች ደግሞ መንግስት የግድያ ወይም የእሥር እርምጃን ካላቆመ አገሪቷን ቀውስ ውስጥ ሊከት እንደሚችል አስጠንቅቀዋል ።

መርጋ ዮናስ

ሕሩት መለሰ