1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቁጠባ እቅድና ተቃዉሞ በግሪክ

ሐሙስ፣ ሰኔ 23 2003

የግሪክ ምክር ቤት ጠንካራ የተባለዉን የቁጠባ እቅድ ትናንት አጽድቋል። ተቃዉሞዉም ግን አላባራም።

https://p.dw.com/p/RWp5
ምስል picture alliance/dpa

የቀረጥ ጭማሪና የወጪ ቅነሳን ያስከትላል የተባለለት እቅድ መፅደቁ አንድ ርምጃ ቢባልም አገሪቱ ቀዉስ ዉስጥ ከገባች ወዲህ የተነሳዉ ተቃዉሞና አመፅ ተባብሶ ቀጥሏል። የአገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን በትናንትናዉ ዕለት ብቻ በፀጥታ ኃይሎችና በተቃዋሚዎች መካከል በነበረዉ ግጭት ከሁለት መቶ ሰዎች በላይ መጎዳታቸዉን ዘግበዋል። ምክር ቤቱ ዛሬም የቁጠባ እቅዱን ተግባራዊ በሚያደርግበት መንገድ ላይ ድምፅ ይሰጣል። የዶቼ ቬለዋ አና ኮክትሲዶ ከአቴና ለዘገበችዉ ሸዋዬ ለገሠ።

አና ኮክትሲዶ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ