1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የበርሊኑ የባህል መተዋወቅያ መድረክ

ሐሙስ፣ የካቲት 24 2003

Black History Month ማለት የጥቁር ህዝቦች ታሪክ ማዉሻ ባህልን መተዋወቃያ ወር በሚል ባለፈዉ የፈረንጆቹ ወር በጀርመን መዲና በበርሊን የተለያዩ አፍሪቃዉያን ያላቸዉን ዕዉቀት በሙዚቃዉም ሆነ በአመጋገብ ባጠቃላይ የተለያየ አፍሪቃቂ ባህልን ያስተዋወቁበት ሆኖ ሰንብቶአል።

https://p.dw.com/p/R5zV
ምስል Jimas Sanwidi

እ.አ 1875 አ.ም በባርነት ከአፍሪቃ ወደ አሜሪካ ከተወሰዱ ቤተሰቦች የተወለዱት ጥቁር አሜሪካዊ ካርተር ዉድሰን እ.አ 1926 አ.ም የጥቁሮች ታሪክ መተዋወቅያ ሳምንት በሚል አፍሪቃዊ ታሪክን እና ባህል ለአሜሪካዉያን ለማስተዋወቅ የጀመሩት መሆኑ ጽሁፎች ያስረዳሉ። በዚህም በዮናይትድ ስቴትስ እና በሌሎች ምዕራባዉያን አገሮች በየአመቱ በየካቲት ወር ላይ የአፍሪቃ ታሪክ ወር በሚል ይታወሳል። በበርሊን በተደረገዉ ዝግጅት ላይ የታሪክ ተራማሪዉ አቶ ፋሲል ተስፋዪ ተገኝተዉ የጀርመን የቅኝ ግዛት አገሮች የህክምና ጥናት ታሪክ በሚል የጥናት ጽሁፋቸዉን
አቅርበዉ ነበር። በለቱ ጥንቅራችን ስለ በርሊኑን ባህል መተዋወቅያ መድረክ እንዲሁም ኢትዮጽያዊዉን የታሪክ ተመራማሪ አነጋግረናል። ሙሉዉን ጥንቅር ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ