1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የበርሊኑ የእስልምና ጉባኤና የሚኒስትሩ አስተያየት

ማክሰኞ፣ መጋቢት 27 2003

የጀርመን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር “ የእስልምና ጉባኤ’ በማለት የሚጠራው ጀርመን የሚኖሩ ሙስሊሞችና የመንግስት ተወካዮች የሚወያዩበት ሶስተኛ ጉባኤ ባላፈው ሳምንት በርሊን ውስጥ ተካሂዷል ።

https://p.dw.com/p/RFdD
ሚኒስትሮቹ ሽቫንና ፍረድሪሽ በጉባኤው ላይምስል dapd
የአሁኑ ጉባኤም ከወትሮው በተለየ የብዙዎችን ትኩረት የሳበና ያነጋገረም ነበር ። የዚህ ምክንያቱም አዲሱ የጀርመን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሀንስ ፔተር ፍሪድሪሽ እስልምና የጀርመን አካል ነው የሚለው አባባል መሰረት የለውም ሲሉ የሰጡት አስተያየት ክርክር ባስነሳ ሰሞን ጉባኤው መካሄዱ ነበር ። ሆኖም ሚኒስትሩ ጉባኤው ከመጀመሩ አስቀድሞ በዚህ አባባላቸው ለማለት የፈለጉትን በማብራራት የተፈጠረውን ቅሬታ ለማርገብ ሞክረዋል። የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን የጀርመን የእስልምና ጉባኤና የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስተያየት ያስከተለውን ቅሬታ ይዳስሳል ። ሂሩት መለሰ አርያም ተክሌ