1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የበርሊን ዓለም አቀፍ ትርዒት

ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 2 2002

በትርዒቱ ዘመኑ ያፈራቸው የመዝናኛና የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች ታይተዋል። ተመልካቹ አድናቆቱን አሳይቷል።

https://p.dw.com/p/P6Od
ምስል Picture-Alliance

በርሊን ውስጥ ካለፈው ዓርብ ጀምሮ አንድ ዓለም ዓቀፍ ትርዒት ተከፍቷል። እስከ ነገ የሚቆየው በሚዘልቀው በዚሁ ዓለም ዓቀፍ ትርዒት የመገናኛ ና የመዝናኛ የስነቴክኒክ ውጤቶች ለዕይታ ቀርበዋል። ትርዒቱ በሰፊው በመጎብኘት ላይ ሲሆን የስቱዲዮ መሳሪያዎች ቴሌቪዥንና ካሜራ የቤት ቁሳቁሶች ማቀዝቀዢያዎች የልብስ ማጠቢያ መሳሪያዎች በጎብኚዎች አድናቆትን አግኝተዋል። እነዚህ በመጎብኘት ላይ ያሉት ድንቅ የመገናኛና የመዝናኛ መሳሪያዎች ኤሌክትሪክና ውኃ እንዲቆጥቡ ተደርገው የተሰሩ ናቸው። ይልማ ሃይለሚካዔል።