1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የበርሊን የገና ገበያ ጥቃት

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 11 2009

በጀርመን መዲና፣ በርሊን  ማዕከል ትናንት ማታ በአንድ የገና ገበያ በተጣለ ጥቃት ቢያንስ 12 ሰዎች ተገድለው ወደ 50 የሚጠጉ መቁሰላቸውን የጀርመን የሀገር አስተዳደር ሚኒስቴር ባለሥልጣናት አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/2Ubwz
Deutschland Merkel und weitere Kabinettmitgleider legen Blumen an Anschlagsort nieder
ምስል Reuters/H. Hanschke

አደጋው የደረሰው አንድ የጭነት ተሽከርካሪ ሕዝብ በተሰበሰበበት የገበያ ቦታ ገብቶ ህዝብ በገጨበት ጥቃት መሆኑን የጸጥታ ኃይላት አስታውቀዋል። የበርሊንን ጥቃት የሽብር ጥቃት ነው አይደለም ምርመራው ቀጥሎዋል። ጥቃቱን ተከትሎም ጀርመን የተለያዩ የጸጥታ ጥበቃ ርምጃዎች እየወሰደች ነው።

ትናንት ማታ በበርሊን  ማዕከል  ስለተጣለው ጥቃት የተለያዩ ሀገራት እና ወገኖች፣ ፈረንሳይ እና የአውሮጳ ህብረትን ጨምሮ  ለጀርመን መንግሥት እና ሕዝብ ሀዘናቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው። 

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሀይማኖት ጥሩነህ/ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ