1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቡሩንዲ መንግሥት እና ስደተኞችን የመመለስ እቅዱ

ቅዳሜ፣ የካቲት 11 2009

ዩጋንዳ በሃገሯ የሚገኙ በብዙ ሺዎች የሚገመቱ የቡሩንዲ ስደተኞችን ወደ ትውልድ ሃገራቸው እንዲመለሱ ልትጠይቅ እንደምትችል አስታወቀች። የዩጋንዳ መንግሥት ይህን ይፋ ያደረገው በቡሩንዲ ሰላም መስፈኑንn ከሃገሪቱ መንግሥት ማረጋገጫ ዋስት ካገኘ በኋላ ነበር።

https://p.dw.com/p/2XmR5
Tansania - Flüchtlinge aus Burundi
ምስል DW/K. Tiassou

burundi refugees for soa cms - MP3-Stereo

ከ45,000 የሚበልጡ የቡሩንዲ ስደተኞች በወቅቱ  በምዕራባዊ ዩጋንዳ የዚዚንጊሮ ወረዳ ባለው የናኪቫል  መጠለያ ጣቢያ ይኖራሉ። ከነዚሁ መካከል ከግማሽ  የሚበልጡት የቡሩንዲ ፕሬዚደንት ፒየር ንኩሩንዚዛ ለሶስተኛ ዘመነ ስልጣን እንደሚወዳደሩ  እጎአ ሚያዝያ፣ 2015 ዓም ካስታወቁ በኋላ በተፈጠረው ውዝግብ ሰበብ ሸሽተው ዩጋንዳ የገቡ ናቸው።

Burundi Pierre Nkurunziza
ምስል picture-alliance/dpa/C. Karaba

የቡሩንዲ መንግሥት አሁን በጎረቤት ዩጋንዳ፣ ታንዛንያ እና ዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ ውስጥ በስደት ያሉት ዜጎቹ እንዲመለሱ የማግባባት ስራ ጀምሯል።
 በዚሁ መሰረትም፣ የቡሩንዲ የሃገር አስተዳደር ሚንስትር ፓስካል ባራንዳጊየ ከጥቂት ቀናት በፊት ወደ ዩጋንዳ በመሄድ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎችን ጎብኝተዋል።  
ሚንስትሩ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ አንዳንዶቹ ስደተኞች ወደ ቡሩንዲ ለመመለስ ጥያቄ አቅርበዋል።
« እርግጥ ነዉ ወደ ትዉልድ ሃገራቸዉ በተቻለ ፍጥነe እንዲመለሱ ነዉ የምንፈልገዉ። በቡሩንዲ የሰላሙ ሂደት መነቃቃቱን ለማሳመን እየሞክርን ነዉ። ይህን ገሃድ አምነዉ ያልተቀበሉትን ለማግባባት ጥረታችንን ሳንደክም እንቀጥላለን። በዚሁ ጥረታችን ላይ የጋዜጠኞች ድጋፍ ያስፈልገናል። የስደት ኑሮ ጥሩ አይደለም። በስደተኞች መጠለያ ጣብያዎች የሚኖሩት ሰዎች ጥፋተኞች አይደሉም፤ የሕግ ክትትል የለባቸዉም። እና ቢመለሱ ጥሩ ነዉ። በዩጋንዳ የሚገኙ አንዳንድ የመጠለያዉ ጣብያ ነዋሪዎች ወደ ትዉልድ ሃገራቸዉ መመለስ እንደሚፈልጉ እናዉቃለን። በታንዛንያ ስደተኞች መጠለያ ጣብያ ያሉት ዜጎቻችንም ወደ ሃገራቸዉ እንዲመለሱ ወደዚያ በመሄድ ለማግባባት የመሞከር እቅድ አለን።»ይሁን እንጂ፣ የቡሩንዲ መንግሥት ተቃዋሚዎች የሃገራቸው መንግሥት የጀመረውን ጥረት ለማሰናከል መንቀሳቀሳቸው እንደማይቀር ሚንስትር ባራንዳጊያ ገልጸዋል። ስደተኞቹ በተለይ፣ ለቡሩንዲ በአሩሻ ታንዛንያ የሰላም ስምምነት ከመፈረሙ በፊት  ወደ ትውልድ ሃገራቸው መመለስ እንደሌለባቸው ነው ተቃዋሚዎች የሚያስታወቁት።
«የሚያሳዝነዉ የጣብያዎቹን ጉብኝታችንን ስናበቃ ወደዚያ በመሄድ ስደተኞቹ ወደ ቡሩንዲ እንዳይመለሱ ለማከላከል የሚሞክሩ ሰዎች አይጠፉም። »
የዩጋንዳ የአደጋ መከላከያ ሚንስትር ሂለሪ ኦኔክ እንዳስታወቁት፣ ወደ ቡሩንዲ መመለስ የማይፈልጉ ስደተኞች በዩጋንዳ ለተወሰነ ጊዜ ብቻ መቆየት ይችላሉ፣ ከዚያ ወደ ቡሩንዲ መመለስ አለባቸው። «የቡሩንዲ መንግሥት ለሕዝቡ ያለዉን ፍቅርና ትኩረት እያሳየ ነዉ። ሕዝቡ ወደ መኖርያ ቤቱ «ሀገሩ» እንዲመለስ ይፈልጋል። በቡሩንዲ ሰላም ከሰፈነ በአሩሻ ታንዛንያ በተጀመረዉ ድርድር ስምምነት ላይ ከተደረሰ በኋላ የስደተኝነቱን አቋም ይዘዉ መቀበል የሚፈልጉትን ለፍልሰትና ስደት ጉዳይ መሥራያ ቤት እናስረክባለን። ዩጋንዳ ዉስጥ የመቆያ የሦስት ወር ቪዛ ነዉ የሚያገኙት፤ ያ  ፈቃዳቸዉ ሲያበቃ እንደ ዩኤስ አሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባናባርራቸዉም ሃገራችንን ለቀዉ እንዲወጡ እንፈልጋለን። ለሃገራቸዉ ዉዝግብ ሰላማዊ መፍትሄ ከተገኘ በኋላ ወደ ሃገራቸዉ ይመለሳሉ ብለን እንጠብቃለን። የሃገራችንን የፍልሰት ፖሊሲ ማክበር ይኖርባቸዋል። አካሄዱ እንዲህ ነዉ። »
 ይሁን እንጂ፣ ሚንስትር ኦኔክ ያሉት ምክትላቸው ሙሳ ኤስዌሩ የሚሉትን ይፃረራል።  እንደ ኤሴዌሩ ማንም ስደተኛ በግዳጅ ወደ ትውልድ ሃገሩ መመለስ የለበትም፣ በዓለም አቀፍ ሕግ  መሰረት፣ 
«  ስደተኞችን በሚመለከተዉ ሕግ መሠረት አንድ ስደተኛ ወደ ትዉልድ ሃገሩ የሚመለሰዉ በዉዴታ ነዉ። ካለ ፈቃዱ እንዲመለስ አይገደድም ። ለመመለስ ከፈለገ ክብሩ ተጠብቆ መሆን አለበት።  »
ዩጋንዳ እና ታንዛንያ በአፍሪቃ ህብረት ጥያቄ መሰረት፣ በአሁኑ ጊዜ በአሩሻ ታንዛንያ የተጀመረውን ለቡሩንዲ ውዝግብ መፍትሔ የሚያፈላልገውን የሰላም ድርድር ይመራሉ። በሮቿን ለስደተኞች ክፍት ባደረገችው ዩጋንዳ ውስጥ ከቡሩንዲ በተጨማሪ፣ ከሶማልያ፣ ርዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን እና ዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ የሄዱ ከ500,000 በላይ ስደተኞች ይገኛሉ።

Karte Ostafrikanische Gemeinschaft Englisch


አርያም ተክሌ

ማንተጋፍቶት ስለሺ